በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናዳ የተያዙ የደላንታ ወረዳ ኦፓል አምራቾች ፍለጋ ተቋረጠ


በናዳ የተያዙ የደላንታ ወረዳ ኦፓል አምራቾች ፍለጋ ተቋረጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

በናዳ የተያዙ የደላንታ ወረዳ ኦፓል አምራቾች ፍለጋ ተቋረጠ

በቁፋሮ ላይ በነበሩበት ዋሻ ውስጥ በናዳ የተያዙ የደላንታ ኦፓል አምራቾችን ሕይወት የመታደጉ ጥረት፣ ከትላንት በስቲያ የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ እንደተቋረጠ፣ አባላቱ በናዳው የተያዙበት የዋሻ ወርቅ ኦፓል አምራቾች ማኅበር አስታወቀ።

የማኅበሩ ሊቀ መንበር ተስፋዬ አጋዥ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስታወቁት፣ ፍለጋው ከስድስት ቀናት ጥረት በኋላ የተቋረጠው፣ በደለል የተሞላውን ዋሻ ለመቦርበር የሚደረገው ርብርብ ሌላ ናዳ በማስከተሉ ነው፡፡

ዋሻው የተናደባቸውን ሰዎች ሕይወት ለመታደግ አልያም አስከሬናቸውን ለማውጣት እንዲመች፣ የተንጠለጠለው የገደሉ አፋፍ በመድፍ ጥይት እንዲመታ ሊቀ መንበሩ ጠይቀዋል።

በደላንታ ወረዳ ዋሻ የተናደባቸውን የኦፓል አምራቾች ለመታደግ ጥረቱ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00

የወረዳው ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ ግን፣ እንዲህ ዓይነቱ ርምጃ የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት የከፋ ስለሚኾን በአማራጭነት እንዳልተጠቀሙት አስረድተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የተቋረጠውን የኦፓል አምራቾቹን ፍለጋ ለማስቀጠል፣ የባለሞያ ቡድን ወደ ስፍራው እንደተላከ፣ የደቡብ ወሎ ዞን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ዛሬ አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG