በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደላንታ ወረዳ በናዳ የተዋጡ ኦፓል አምራቾችን ሕይወት የመታደግ ጥረት አራተኛ ቀኑን ይዟል

በደላንታ ወረዳ በናዳ የተዋጡ ኦፓል አምራቾችን ሕይወት የመታደግ ጥረት አራተኛ ቀኑን ይዟል

በደላንታ ወረዳ በናዳ የተዋጡ ኦፓል አምራቾችን ሕይወት የመታደግ ጥረት አራተኛ ቀኑን ይዟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:06 0:00

በደላንታ ወረዳ በናዳ የተዋጡ ኦፓል አምራቾችን ሕይወት የመታደግ ጥረት አራተኛ ቀኑን ይዟል

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፣ ሰው ሠራሽ ዋሻ የተናደባቸውን ኦፓል አምራቾች ሕይወት ለመታደግ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ ዛሬ አራተኛ ቀኑን እንደያዘ፣ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በቀበሌ 018 ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፣ ኦፓል በማምረት ላይ ሳሉ የተቆፈረው ዋሻ በመደርመሱ በናዳ የተያዙ ወጣቶችን ሕይወት ለመታደግ፣ ተጨማሪ የሰው ኃይል በቁፋሮ ሥራ ላይ እንደተሰማራ፣ የወረዳው የብልጽግና ጽ/ቤት ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ፣ ከገደሉ ጫፍ ወደ ውስጥ 30 ሜትር ገደማ በሰው ጉልበት መቆፈሩ ታውቋል፡፡

እስከ አሁን የተገኘ ምልክት ባይኖርም፣ “በሕይወት እናገኛቸዋለን፤” ያሉ ቤተሰቦቻቸውና በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በአደጋው ስፍራ በነፍስ አድን ጥረቱ እየተረባረቡ እንደሚገኙ፣ አንድ የቤተሰባቸው አባል በናዳው የተያዙባቸው አስተያየት ሰጭ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG