በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደላንታ ወረዳ በናዳ ለተቀበሩ ኦፓል አምራቾች የነፍስ አድን ጥረቱ አምስተኛ ቀን ሆነው


በደላንታ ወረዳ በናዳ ለተቀበሩ ኦፓል አምራቾች የነፍስ አድን ጥረቱ አምስተኛ ቀን ሆነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

በደላንታ ወረዳ በናዳ ለተቀበሩ ኦፓል አምራቾች የነፍስ አድን ጥረቱ አምስተኛ ቀን ሆነው

በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት በዋሻ ውስጥ በቁፋሮ ላይ ሳሉ በናዳ የተያዙ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ የሚደረገው ጥረት፣ ዛሬ አምስተኛ ቀኑን እንደያዘ፣ የወረዳው ማዕድን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት የጽ/ቤቱ ኃላፊ፣ እስከ አሁን የተገኘ ምልክት ባይኖርም የአካባቢው ማኅበረሰብ ከ70 ሜትር በላይ ወደ ተራራው ውስጥ በመቆፈርና የተናደውን በማንሳት ሰዎቹን በሕይወት ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው፤ ብለዋል፡፡

አንድ የከተማዋ ነዋሪ፣ ባህላዊ ማዕድን አምራቾቹ ከቆፈሩት የዋሻው ርዝመት የተነሣ ሊደርስ ከሚችለው መታፈን፣ ሊያጋጥም ከሚችለው የምግብ እና የውኃ እጥረት አንጻር፣ ዋሻው የተናደባቸውን ሰዎች በሕይወት ለመታደግ ሊያዳግት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ብዙዎቹ ነዋሪዎች እና ቤተሰቦች ደግሞ፣ ከተመሳሳይ አደጋ ከዚህ ቀደም የተረፉ እንደነበሩ በማስታወስ ጥረታቸውን በተስፋ እንደቀጠሉ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG