በኬንያ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሥርዓት ላይ የሚደረግ የተሃድሶ ለውጥ በሁለቱ ጎራ ላሉትወገኖች መደራደሪያ ሊሆን እንደሚችል ተገለጠ።
ባለፈው ወር ተቃዋሚ ወገኖች የተጠሯቸው በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች በግጭት ቢጠናቀቁም፤በዛሬው ዕለት በተካሄደው የናይሮቢው ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተናገሩት የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga ድርድሮች በሚካሄዱበት መንገድ ላይ ያተኮሩ ዕቅዶች በመነደፍ ላይ መሆናቸውንገልጠዋ።
የኬንያ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የዛሬውን የነጻነት ቀን ለማሰብ ናይሮቢ ላይ ሰላማዊ ሰልፍአካሂደዋል።
እውነትና ፍትህ እንዲረጋገጥ እንሻለን። ለዚህም ነው የምርጫ ኮምሽኑ ሊቀመንበር ኃላፊነታቸውን በፍጥነት ለማስረከብ መዘጋጀት አለባቸው፤ የምንለው።”የተቃዋሚው መሪ Raila Odinga
በብዙ ሺህ ለተቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉት የዋናው የተቃዋሚዎች ሕብረት፤በእንግሊዝኛው ምሕጻረ-ቃል CORD መሪ Raila Odinga በኬንያ የምርጫ ማስፈጸሚያ ሥርዓትላይ ለሚደረግ የተሃድሶ ለውጥ ሁለቱ ወገኖች፤ (የኬንያ መንግስትና ተቃዋሚዎች) እስከ አርብ ባለውጊዜ አምስት-አምስት የፓርላማ አባላቶችን በየበኩላቸው ለመወከል መስማማታቸውን ይፋአድርገዋል።
ተቃዋሚዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ያለመቀየራቸውንና ዘጠኙ የምርጫ ኮምሽን አባላትም ከኃላፊነትእንዲወርዱ መጠየቃቸውን ኦዲንጋ አስረድተዋል።
Lenny Ruvaga ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል።