በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደህንነት መሥሪያ ቤቱ የኮሎኔል ደመቀን የስልክ ንግግር በድምፅ እንዲያመጣ ታዟል


የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በፌስ ቡክ የሚዘዋወር ፎቶ
የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በፌስ ቡክ የሚዘዋወር ፎቶ

የብሔራዊ ደኅንነት እና መረጃ አገልግሎት ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ስልክ ላይ ቀድቸዋልሁ በሚል በጹሑፍ ያቀረበውን ሪፖርት በጽምጽ ያቅርብ ሲል የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ። ከኮሎኔሉ ጋር ስለ ሽብር ያወራሉ የተባሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ቁጥርም እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የደህንነት መሥሪያ ቤቱ የኮሎኔል ደመቀን የስልክ ንግግር በድምፅ እንዲያመጣ ታዟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ ከወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አባላት መካከል አንዱ ሲኾኑ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ነው ከጎንደር ከተማ ተይዘው የታሰሩት። ጉዳዩን የያዘው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደሕንነት መሥሪያ ቤቱ በጹሑፍ የሰጠውን ማስረጃ በድምፅ ያቅርብ ሲል ከሦስት ቀናት በፊት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ይህንን ትዕዛዝ የሰጠው ጠበቆቹ በዓቃቤ ሕግ ማስረጃ ላይ ተቃውሞ በማቅረባቸው ነው። ከኮሎኔል ደመቀ ጠበቆች አንዱ የሆኑት አቶ አለልኝ ምሕረቱ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፤ ፍርድ ቤቱ ለጥቅምት 27 ቀን ቀጥሮ የነበረው ዓቃቤ ሕግ "ማስረጃዎቼን አሰምቼ ጨርሻለሁ" በማለቱ ለብይን ነበር።

ነገር ግን ጠበቆቹ ብይን ከመሰጠቱ በፊት በዓቃቤ ሕግ ያቀረብው የሰነድ ማስረጃ የድምፅ ማስረጃ ይቅረብበት ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል። ይህ ሰነድ የቀረበው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከስልክ ምልልስ ያገኘሁት ነው ብሎ ያዘጋጀው ሪፖርት ሲሆን ጠበቆቹ የስልኩ ንግግርየኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ያደረጉት ከሆነ በቀጥታ የድምፅ ማስረጃው ይቅረብልን ሲሉ ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የቀረበው ተቃውሞ ተገቢ እንደሆነ በመግለፅ የድምፅ ማስረጃው ይቅረብ ብሏል።በተጨማሪም ከኮሎኔሉ ጋር ስለ ሽብር ያወራሉ የተባሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ቁጥርም እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የደህንነት መሥሪያ ቤቱ የኮሎኔል ደመቀን የስልክ ንግግር በድምፅ እንዲያመጣ ታዟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG