በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬዥ የዓለምን የአየር ንብረት በሚመለከት አስጠነቀቁ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ግብጽ ሻርም ኤል ሼኽ ላይ ቀጥሏል።

ትናንት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ የተደቀነውን ጥፋት ለመቀልበስ የዓለም ሀገሮች በተለይም ባለጸጎቹ ሀገሮች ፈጥነው ዕርምጃ እንዲወስዱ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ለሚመራው ጉባዔ ባደረጉት ንግግር "ወደአየር ንብረት ገሃነመ እሳት በአንዳች ፍጥነት እየበረርን ነን” ያሉት ጉቴሬዥ “የምንታገለው ለህልውናችን ስንል ነው፤ እየተሸነፍንም ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዘንድሮው ጉባዔ ዋናው መነጋገሪያ አጀንዳ ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ዋናዎቹ የበካይ ጋዝ አመንጪ የሆኑት ባለጸጎቹ በኢንዱስትሪ ያደጉት ሀገሮች የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያደርሰው ጉዳት በይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑት ደሆቹ ሀገሮች እንዴት እና ምን ያህል ድጋፍ መስጠት አለባቸው የሚለው እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ከሁለት መቶ በላይ ሀገሮች ተወካዮች ለዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በግብጽ ሻርም ኤል ሼኽ ይገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG