በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና እና ጃፓን የስትራቴጂክ ግንኙነታቸውንና ለሰላም የጋራ ኃላፊነታቸው ስለማረጋገጥ ተነጋገሩ


የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሳን ፍራንሲስኮ የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ ላይ
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሳን ፍራንሲስኮ የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ጉባኤ ላይ

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር ትናንት ሐሙስ በሳን ፍራንሲስኮ በተካሄደው የእስያ-ፓሲፊክ ኢኮኖሚ ትብብር (APEC) ኢኮኖሚዎች ጉባኤ ላይ ተገናኝተው ተነጋገሩ።

ሺ ከጃፓን ጋር "ስትራቴጂካዊ እና የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነታችንን" ያሉትን በድጋሚ እንዲረጋረጥ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ኪሺዳ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት ለዓለም አቀፍ ሰላም እና ብልጽግና "የጋራ ኃላፊነት" እንዳላቸው ተናግረዋል ።

ሺ ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ከዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ቆይታ ያደረጉ ሲሆን ይህም በአንድ ዓመት ውስጥ ፊት ለፊት ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜያቸው ነው፡፡

የቻይናው መሪ በተጨማሪ ከሜክሲኮ፣ ፔሩ፣ ፊጂ፣ እና ብሩኔ መሪዎች ጋርም በግል ተወያይቷል።

ዓመታዊው ጉባኤ የሀገራት መሪዎች እና ሌሎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ መሪዎችን አንድ ላይ የሚያገናኝ መድረክ ነው፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG