በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ከአሜሪካ ጋር መካረር አትፈልግም - ተንታኞች


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ሳን ፍራንሲስኮ ላይ ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ቤጂንግ ከዋሽንግተን ጋር የገባችበትን ውጥረት ለማርገብ ስትል ፍጥጫ የማይጋብዝ አቀራረብ መምረጧ ተነገረ።

“ቻይና በዓለም ዙሪያ ባላት ሥፍራ ከዩናይትድ ስቴትስ ለመብለጥ ወይም ለመተካት ዕቅድ እንደሌላት፣ እንዲሁም ቤጂንግ የምትከተለውን ርዕዮተዓለም ወደ ሌሎች ሃገሮች ማዛመት እንደማትሻ ሺ ማመልከታቸውን በይፋ የቀረበው ሰነድ ያሳያል” ሲሉ የዓለም ፖለቲካ አዋቂዎች ተናግረዋል።

በትናንቱ (ረቡዕ) የሁለቱ መሪዎች ስብሰባ ወቅት ቻይና ያንፀባረቀችውን አቋም ለአሜሪካ ድምፅ ያብራሩት የአውስትራሊያው ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዌን-ቲ ሱንግ ሲናገሩ “በጉባዔው የተላለፉት መልዕክቶች ‘ምሥራቁ ከፍ እያለ ምዕራቡ እየወደቀ ነው’ ከሚለው ሺ ይዘውት ከነበረው ሃሳብ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው” ብለዋል።

ቤጂንግና ዋሽንግተን ፍጥጫና ውጥረትን ማስወገዳቸው አስፈላጊ መሆኑን ሺ አመልክተው ሁለቱ ኃያላን አንዳቸው በሌላኛው ላይ “ፊታቸውን ማዞር” እንደ አማራጭ የሚወስዱት መሆን እንደማይገባው መክረዋል።

"ቻይና የገጠሟት የኢኮኖሚ ፈተናዎች በውጭ ፖሊሲዋ ከምታራምደው እሳቤ ጋር መጋጨት የጀመረ ይመስላል” ሲሉ ተንታኙ አክለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG