ዋሽንግተን ዲሲ —
አብዛኛውን ቻይናውያን ጥንዶች፤ ከአንድ ልጅ በላይ እንዳያፈሩ የሚያስገድደውና ሰላሳ አምስት ዓመታት ያስቆጠረው ሕግ ተሻረ። በዛሬው እለት የቻይና ኮሚንስት ፓርቲ ይፋ ያደረገው ይህ አዲስ ፖሊሲ ቻይናውያን ቤተሰቦች ያለ አንዳች መቀጮ ሁለት ልጆችን ማፍራት እንዲችሉ ይፈቅዳል።
አንዳንዶች በአንድ ልጅ ብቻ ተገድበው ለኖሩ ቤተሰቦች የተሻለ ምልዓት በሚያስጎናጽ ሁነኛ እርምጃ ሲመስሉት፤ ሌሎች ግን፤ መንግስት የሚጠብቀውን ፈተና አጉልተው በማውሳት የፖሊሲ ለውጡ ሊከስት ይችላል ባሉት የምጣኔ ሃብት ሁኔታ ላይ ማተኮር መርጠዋል።
የፖሊሱ ለውጡ ራሱ ይበልጡን እያደገ በመጣው በአገሪቱ የምጣኔ ሃብት ይዞታ ላይ ከተደቀነው ግፊት የመጣ መሆኑ ነው የተዘገበው።