በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዊኪሊክሱ ጁሊያን አሳንጅ ተላልፎ እንዳይሰጥ ሕጋዊ ጥረት በማደረግ ላይ ነው


የዊኪሊክስ መሥራች የሆነው ጁሊያን አሳንጅ ደጋፊዎቹ ከችሎቱ ውጪ ሰልፍ አድርገው፣ እንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት፤ የካቲት 21/2024
የዊኪሊክስ መሥራች የሆነው ጁሊያን አሳንጅ ደጋፊዎቹ ከችሎቱ ውጪ ሰልፍ አድርገው፣ እንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት፤ የካቲት 21/2024

የዊኪሊክስ መሥራች የሆነው ጁሊያን አሳንጅ ከእንግሊዝ ወደ አሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ በዚህ ሳምንት የመጨረሻ ሕጋዊ ሙከራ በማድረግ ላይ ነው።

የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ሚስጢሮችን የያዙ ሰነዶችን በዊኪሊክስ ድህረ ገፅ ላይ ለሕዝብ ይፋ በማድረጉ የስለላ ክስ የተመሠረተበት ጁሊያን አሳንጅ፣ በሕመም ላይ በመሆኑ፣ በእንግሊዙ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባይገኝም፣ ደጋፊዎቹ ከችሎቱ ውጪ ሰልፍ አድርገዋል።

አሳንጅ ተሰርቀው የመጡለትን የአሜሪካ ሚስጥራዊ ሰነዶች ለህትመት በማብቃቱ ያደርገው ነገር ቢኖር፣ የጋዜጠኝነት ሥራውን ማከናወኑ ብቻ እንደሆነ፣ ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ በተደረገው ክርክር ላይ ጠበቆቹ ለችሎቱ አስረድተዋል።

በተለይም የጦር ወንጀሎችን እና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለህትመት ማብቃቱ፣ ሕዝብ ማወቅ ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን እና ሃሳብን በነጻ ከመግለጽ መብት ጋር የሚያያዙ ናቸው ሲሉ ጠበቆቹ ተከራክረዋል።

አሜሪካ 18 የሚሆኑና፣ “ሚስጥራዊ ሰነዶችን በመጥለፍ እና በመሥረቅ” የሚሉ የፌዴራል ክሶችን አሳንጅ ላይ አቅርባለች፡፡ የአሜሪካን ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ የጣለ ነው ስትልም ትከራከራለች፡፡

አውስትራሊያዊው አሳንጅ በቅድሚያ በእንግሊዝ የተያዘው ከ14 ዓመታት በፊት ሲሆን፣ ስዊዲን ውስጥ ፈጽሞታል በተባለ የጾታዊ ጥቃት ክስ ነበር። ዋስትናውን በመጣስ በኢኳዶር ኤምባሲ በጥገኝነት ተጠልሎ ለዘጠኝ ዓመታት ከቆየ በኋላ፣ በእ.አ.አ 2019፣ ከአምስት ዓመታት በፊት፣ ከኤምባሲው እንዲወጣ ተደርጎ በእንግሊዝ ቁጥጥር ሥር ውሏል።

ከሁለት ዓመታት በፊት፣ በሰኔ 2022፣ አሜሪካና እንግሊዝ የአሳልፎ መስጠት ስምምነት ተፈራርመዋል።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለመስጠት በርካታ ቀናት ወይም ሳምንታት እንደሚወስድበት ይጠበቃል።

አሳንጅ ወደ ትውልድ አገሩ መመለስ እንዲፈቀድለት የአውስትራሊያ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ጥሪ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG