በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በአሳንጅ ላይ ክስ መሰረተች


WikiLeaks founder Julian Assange arrives at the Westminster Magistrates Court, after he was arrested in London, Britain April 11, 2019.
WikiLeaks founder Julian Assange arrives at the Westminster Magistrates Court, after he was arrested in London, Britain April 11, 2019.

ድብቅ የመንግሥታት ገበናዎችን በበይነ መረብ ላይ በመበተን የሚታወቀው ዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡አሳንጅ ወሲባዊ ጥቃት አድርሰዋል በሚል በስዊድን ክስ ከተከፈተባቸው ወዲህ ላሉት ሰባት ዓመታት እንግሊዝ ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ ተሸሽገው ነበር፡፡

ኢኳዶር አሳንጅ ከዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የቀን ተቀን የሕይወት መርሆችን ተቃራኒ የሆኑ አድራጎቶችን በመደጋገማቸው ከዚህ በኋላ ከለላ እንደማትሆናቸው በፕሬዚደንቷ ሌኒን ሞሪኖ በኩል አሳውቃ ነበር፡፡

የ47 ዓመቱ ጁሊያን አሳንጅ ለስዊዲን ተላልፈው ከተሰጡ፣ በአሜሪካ እጅ ሊገቡ እንደሚችሉ በመግለጽ ሲሟገቱ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

አሳንጅ በተያዙ በሰዓታት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ብዙ መቶ ሺህ የዩናይትድ ስቴትስ ሚስጥራዊ ሰነዶች ከመጋለጣቸው ጋር በተያያዘ “የኮምፒዩተር ሰርስሮ ብርበራ ወንጀል” ክስ መስርታባቸዋለች።

አሳንጅ በተመሰረተባቸውት ክስ ወንጀለኛ ተብለው ከተበየነባቸውት በአምስት ዓመት እስራት ሊቀጡ ይችላሉ። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ዩናይትድ ስቴትስ በአሳንጅ ላይ ክስ መሰረተች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:36 0:00

XS
SM
MD
LG