በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዊኪሊክስ መስራቹ አሳንጅ ለዩናይትድ ስቴትስ ተላልፎ እንዲሰጥ ብሪታንያ ፈቀደች


ፎቶ ፋይል፦ የዊኪሊክስ መስራቹ ጁሊያን አሳንጅ እአአ ግንቦት 1/2019
ፎቶ ፋይል፦ የዊኪሊክስ መስራቹ ጁሊያን አሳንጅ እአአ ግንቦት 1/2019

የብሪታንያ መንግሥት የዊኪሊክስ መስራቹ ጁሊያን አሳንጅ በስለላ ወንጀል ለከሰሰችው ለዩናይትድ ስቴትስ ተላልፎ እንዲሰጥ ፈቀደ። ዊኪሊክስ ይግባኝ እንደሚል አስታውቋል።

የብሪታንያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ፕሪቲ ፓተል አሳንጅ ተላልፎ ይሰጥ የሚል ትዕዛዝ ፈርመዋል። ሚኒስትሯ ትዕዛዙን የሰጡት የብሪታንያ ፍርድ ቤት አሳንጅ ተላልፎ ሊሰጥ ይችላል የሚል ውሳኔ መስጠቱን ተከትሎ ሲሆን የአገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣

"ተላልፎ መሰጠቱ ኢፍትሃዊ ወይም ተገቢ ሂደትን መጣስ እንደማይሆን ፍርድ ቤቶቻችን" ደምድመዋል ብሏል።

አሳንጅ ወደዩናይትድ ስቴትስ እንዳይላክ ለበርካታ ዓመታት ሲታገል የቆየ ሲሆን አሁንም ይግባኝ ለማለት የአስራ አራት ቀናት ጊዜ እንዳለው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG