በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ድንበር የተነሳው አለመስማማት ሰፊ ውጥረት ፈጥሯል


የኢትዮጵያ ሱዳን ካርታ
የኢትዮጵያ ሱዳን ካርታ

ሱዳን የኢትዮጵያ ኃይሎች ድንበር ላይ ወታደሮቼን ይዘው ገለውብኛል ስትል ያቀረበችውና አዲስ አበባ ውድቅያደረገችው ውንጀላ፣ በለም መሬት ምክንያት ለአስርት አመታት የቆየውን ፀብ እንዳዲስ ቀስቅሶታል።

አልፋሽካ በተሰኘው መሬት ዙሪያ ላለው ውዝግብ መላ መጥፋቱ የደቀነው አደጋ የቀጠናውን መሪዎች ያስደነገጠ ሲሆን በመሬት እና ውሃ ምክንያት ተቀናቃኝ የሆኑት ሱዳን እና ኢትዮጵያ መሃከል ያለውን ውጥረትም አስፍቶታል።

ደም አፋሳሽ ግጭት

ያሳለፍነው ሰኞ ካርቱም የኢትዮጵያ ሰራዊት ሰባት ወታደሮቿን እና አንድ ሲቪል በአጨቃጫቂው አልፋሽካ ባለፈው ሳምንት ገድለውብኛ ብላ ክስ ማቅረቧን ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደርሯን ጠርታ እንደምታነጋግር አስታውቃ ነበር።

ሱዳን እንደምትለው ሰኔ 15 ቀን ወታደሮቿ ከድንበሯ ክልል ውስጥ ታግተው ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰዱ በኋላ ተገድለውና አካላቸው ጎሎ በአደባባይ ታይተዋል።

ሁለቱም ሀገሮች የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱበት አጨቃጫቂ የድንበር አካባቢ ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉት የሱዳን ሰራዊት መሪ አብድልፈታህ አል-ቡራን፣ በመሬታቸው ላይ ምንም ዓይነት አዲስ እንቅስቃሴ ወይም መተላለፍ እንዳይፈቅዱ ለወታደሮቻቸው ነግረዋቸዋል።

እ.አ.አ አቆጣጠር በጥቅምት 2021 ዓ.ም ከተካሄደው የመንግሥት ግልበጣ በኋላ በስልጣን ላይ የሚገኘው ሰራዊት "ይህ የሸፍጥ ድርጊት የሚታለፍ አይደለም" ሲል ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ሰራዊት በበኩሉ በተባለው ግድያ ውስጥ እጁ በምንም መልኩ እንደሌለበት በመግለፅ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ትዕዛዝ ከተሰጠው የሱዳን ኃይሎችን ከተያዙ መሬቶች እንደሚያስለቅቅ ቃል ገብቷል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00

አዲስ አበባ፣ የደረሰው አደጋ በአካባቢው ሚሊሺያዎች ጋር በተደረገ ግጭት መሆኑን እና የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው መግባታቸውን ገልፃ ከሳለች።

አዲስ አበባ በበኩሏ የሱዳን ሃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው መግባታቸውንና የሰው ሕይወት የጠፋውም በአካባቢው ከነበሩ ሚሊሺያዎች ጋር በተደረገ ግጭት እንጂ መደበኛ ወታደሮቿ በአካባቢው እንዳልነበሩ በትናንት መግለጫዋ አስታውቃለች።

የሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ሀይሎች መሃከል የሚደረገው ማስፈራራት እየተጠናከረ መሄዱን ተከትሎ የአፍሪካ ኅብረት እና የቀጠራው መሪዎች ሁኔታው እንዲያበርድ ጥሪ እያቀረቡ ነው።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር "ለጋራ ፍላጎቶቻችን እና ለጥሩ ጉርብትናችን ስንል" በሚል በአረብኛ ጽሑፍ ባስተላለፉት መልዕክትም መታቀብንና መረጋጋትን ጠይቀዋል።

በርግጥ ሁለቱ ሀገራት በሚጋሩት ድንበር ላይ በሚገኘው ለም መሬት ምክንያት የተፈጠረው አለመረጋጋት ቀደም ሲል ደርሶ ከነበረው ደም አፋሳሽ ግጭት የራቀ ነው። በኅዳር ወር ላይ ከኢትዮጵያ ሰራዊት ጋር ቁርኝት ያላቸው የታጠቁ ሚሊሺያዎች በአልፋሽካ ላይ ስድስት የሱዳን ወታደሮችን መግደላቸውን ጠቅሶ የሱዳን ሰራዊት የከሰሰ ሲሆን አዲስ አበባ ይህንንም ክስ ውድቅ አድርጋ ነበር።

ደም እና መሬት

በኢትዮጵያ የሚገኙትን የአማራ እና የትግራይ ክልሎች ከሱዳን ገዳርፍ ክልል ጋር በሚያገናኛቸውና በሁለት ወንዞች በተከበበው አል-ፋሽካ መሬት ዙሪያ የሚደረገው እሰጥ አገባ ከቅኝ ግዛት ዘመን የጀመረ ነው።

አልፋሽካ ወደ 12 ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን ባለሞያዎች እንደሚሉት በድንበር አካባቢ የሚገኘው ቁልፍ ዞን 250 ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሆን ቦታ ነው።

ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነት ዓለም ምስራቃዊ የአልፋሽካ ድንበርን ለሱዳን እንዲሆን በማድረግ ዓለም አቀፍ ድንበሩ እንዲካለል አድርጓል።

ከዛ ቀጥሎ ባሉት ዐስርት ዓመታት ግን በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በዝናብ ወቅት አካባቢዎን በማረስ ሰብሎችን ቢያበቅሉበትም በተለያዩ ግዜያት የሱዳን ወታደሮች ከአካባቢው ያባርሯቸዋል።

እ.አ.አ በ1995 በወቅቱ የግብፅ ፕሬዝዳንት የነበሩት ሆስኒ ሙባረክ አዲስ አበባን ሲጎበኙ የተደረገውን የግድያ ሙከራ ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ እና በካርቱም መካከል ያለው ግንኙነት ሻከረ። ለጥቃቱ ሱዳንን ተጠያቂ ያደረገችው ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ወደ አልፋሽካ ላከች።

ከዛን ጊዜ ወዲህ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ገበሬዎች በአካባቢው በመስፈር ለኢትዮጵያ መንግሥት ግብር ይከፍላሉ። በካርቱም እና በአዲስ አበባ መሃከል ለዓመታት የተካሄዱ ድርድሮችም ምንም ዓይነት ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።

ጦርነት እና ውሃ

አልፋሽካ በኢትዮጵያ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኘውና ከጥቅምት 2013 ዓም ጀምሮ በፌደራል ኃይሎች እና በህወሃት መሃከል ደም አፋሳሽ ግጭት ከተካሄደበት የትግራይ ክልል ጋራ ይዋሰናል።

ግጭቱን የሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሱዳን በመግባታቸው በሁለቱ ሀገራት መሃከል ያለውን ውጥረት አባብሶታል። በጦርነቱ ወቅት አብይ በከፍተኛ ሁኔታ የተማመነው በአማራ ክልል ኃይሎች ላይ ቢሆንም፣ ዲፕሎማቶች ለሰላም ንግግሮች ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ በመሃከላቸው አለመግባባት ተፈጥሯል። በርካታ የአማራ ባለስልጣናት አልፋሽካ ሕጋዊ መሬታቸው እንደሆነ የሚያምኑ በመሆናቸው፣ አንዳንድ ተንታኞች ምናልባት አብይ በግዛት ይገባኛል ፍላጎታቸው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ችግር ይገጥመው ይሆናል ብለው ይፈራሉ።

ሱዳንም ሆነ ኢትዮጵያ በሀገራቸው ውስጥ አሳሳቢ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን እያስተናገዱ ነው።

ኢትዮጵያ ከትግራይ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል እና በኦሮሚያ ክልልሎች የሚነሱ ውስጣዊ ሁከቶችን አሉባት። በጥቅምት ወር በተካሄደ የመፈንቅለ መንግስት ቡርሃን ስልጣን በያዙባት ሱዳን ደግሞ የሲቪል አገዛዝ እንዲኖር የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች በኃይል እንዲበተኑ ሲደረጉ ቆይተዋል።

በእርሻ መሬት ላይ የሚካሄደው የድንበር ላይ ይገባኛል ጥያቄ በሁለቱ ሀገራት መሃከል በሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት ዙሪያም ስጋት ይፈጥራል - በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ በምትገነባው ግዙፍ ግድብ ላይ።

የአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገሮች መሃከል አንዷ የሆነችውና በግድቡ አሞላል እና እንቅስቃሴ ዙሪያ አሳሪ ስምምነት እንዲደረስ ግፊት ከምታደርገው ግብፅ ጎን ለጎን ሱዳን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አቅርቦቷን ስጋት ውስጥ ይከታል ብላ ታምናለች።

ኢትዮጵያ ግን ግፊቱን ተቋቁማ በየካቲት ወር ላይ በግድቡ አማካኘነት ኤሌክትሪክ ማመንጨት መጀመሯን አስታውቃለች።

/ዘገባው የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው/

XS
SM
MD
LG