በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ሱዳን ውጥረትን ከማባባስ እንዲታቀቡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጠየቁ


የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ
የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ

በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል “እየተባባሰ የመጣው ወታደራዊ ፍጥጫ” አሳስቦኛል በማለት ሁለቱ ወገኖች እንዲታቀቡና ወደ ንግግር እንዲመጡ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጥሪ አደረጉ።

ሊቀመንበሩ “በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በሱዳን ሪፐብሊክ መካከል እየተባባሰ ያለውን ወታደራዊ ውጥረት በጥልቅ ትኩረት እየተከታተሉ ነው። በሃገራቱ ድንበር አካባቢ የሰው ህይወት በመቀጠፉም ትልቅ ሐዘን ተሰምቷቸዋል” ብሏል ኮሚሽኑን ባወጣው መግለጫ።

መግለጫው የወጣው ካርቱም ሰባት የተማረኩ ወታደሮቼንና አንድ ሲቪል በአጨቃጫቂ የድንበር አካባቢ ባለፈው ሳምንት ገድላብኛለች ስትል ኢትዮጵያን ከከስችና ኢትዮጵያም ክሱን ውድቅ ካደረገች በኋላ ነው።

መግለጫው አያይዞ “ሊቀመንበሩ ሁለቱ ወገኖች ከማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ ሙሉ በሙሉ እንዲቆጠቡና ሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች አጨቃጫቂ ጉዳዮችን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አድርገዋል” ብሏል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት “ወታደሮቼን በድንበር አካባቢ በሚገኝውና አል ፋስካ በተባለው አጨቃጫቂ በሆነው ለም መሬ አካባቢ አግታብኛለች ስትል ሱዳንት ከሳለች።

ካርቱም በኢትዮጵያ የሚገኙትን አምባሳደሯን ሰኞ ዕለት ጠርታ ስታበቃ ለተመድ የጸጥታው ም/ቤትና ለቀጠናው ተቋማት ወቀሳ እንደምታቀርብ አስታውቃለች ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

አዲስ አበባ በበኩሏ የሱዳን ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው መግባታቸውንና የሰው ህይወት የጠፋውም በአካባቢው ከነበሩ ሚሊሺያዎች ጋር በተደረገ ግጭት እንጂ መደበኛ ወታደሮቿ በአካባቢው እንዳልነበሩ በትናንት መግለጫዋ አስታውቃለች።

ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣ የሱዳን ሰራዊት በኢትዮጵያ ላይ ትናንት ማክሰኞ በአል ፋሽካ ጥቃት መሰንዘሩን ቢዘግብም የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ናቢል አብደላ ሪፖርቱን አስተባብለዋል።

“ማንንም አላጠቃንም፣ ማንንም ለማጥቃት ዕቅድ የለንም። የማንም ሀገር ሰራዊት ግን አለም አቀፍ ድንበራችንን ጥሶ እንዲገባ አንፈቅድም። እንዲህ ዓይነቱን ጉዳይ በህጋዊ መንገድ መያዝ መብታችን ነው” ሲሉ ናቢል ለኤ.ኤፍ.ፒ ተናግረዋል።

ለረጅም ግዜ በኢትዮጵያ ገበሬዎች ሲመረትበት በቆየውና በኋላም ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ ባነሳችበት ኣል ፋሻካ በተባለው ለም መሬት ሳቢያ በካርቱምና በአዲስ አበባ መካከል ያለው ግንኙነት አየሻከረ ሲመጣ፥ አልፎ አልፎም በሁለቱ ወገኖች መሃል ግጭቶች ተስተውለዋል። አንዳንዶቹ ግጮቶችም ህይወት ቀጥፈዋል።

የድንበር ጭቅጭቁ በአካቢብው ያለውንና በአባይ ግድብ ግንባታ ምክንያት የተፈጠረውን ሌላ ውጥረት ያባብሰዋል ብሏል የኤፍፒ ሪፖርት።

በታችናው የዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የሚገኙት ሱዳንና ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታካሂደውን የግድብ ግንባታ የሚቃወሙ ሲሆን ግድብ መሙላቱና አጠቃላይ የስራውን ሂደት በተመለከተ ዝርዝር ስምምነት እንዲደረግ ግፊት እያደረጉ ነው።

/ዝርዝሩን ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:45 0:00

XS
SM
MD
LG