በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ውጥረት


የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ውጥረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:23 0:00

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ድንበር ውጥረት

የሱዳን መንግሥት በሁለቱ አገሮች ድንበር ያለውን ውጥረት የበለጠ ከማባባስ እንዲቆጠብ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ።

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለፃ ያደረጉት አቶ ደመቀ አገራቸው የድንበር ውዝግቡን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗንም አስታውቀዋል።

የሱዳን ታጣቂዎች በአብድራፊና በምዕራብ አርማጭሆ በኩል ከፍተውት የነበረው ተኩስ ከትላንት ጀምሮ መቆሙን የገለፁት ደግሞ የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቢሰጥ ወርቄ ናቸው።

የሱዳን ሰራዊቱ ቃል አቀባይ ናቢል አብደላ “ማንንም አላጠቃንም፣ ማንንም ለማጥቃት ዕቅድ የለንም። የማንም ሀገር ሰራዊት ግን አለም አቀፍ ድንበራችንን ጥሶ እንዲገባ አንፈቅድም።” ማለታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG