በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ወደቶኪዮ ተጉዘው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መገደል ሀዘናቸውን ገለፁ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን

በዛሬው ዕለት በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ ጉብኝት ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንክን በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ መገደል ሀዘናቸውን ገለጹ።

ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ ጋር ከተወያዩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "ለጃፓናውያን ባልደረቦቻችን ይህ ሰቅጣጭ ግድያ ባስከተለው ሀዘን እና ድንጋጤ አብረናቸው መሆናችንን ገልጬላቸዋለሁ" ብለዋል። አቤ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው ዘመን የጃፓን እና ዩናይትድ ስቴትስን ግንኙነት አዲስ ደረጃ ላይ ያደረሱ በመሆናቸውም ህልፈታቸው ያሳዝነናል ብለዋል።

የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር አቤ ባለፈው ዐርብ ናራ በተባለች ከተማ የምርጫ ዘመቻ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው ይታወሳል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ወደ ጃፓን የተጓዙት "ከጃፓን ጋር ከአጋርነትም ይበልጥ ወዳጆች በመሆናችን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጉብኝቱን እንዳደርግ በሰጡኝ መምሪያ መሰረት ነው" ብለዋል።

በእስያ ሀገሮች ጉብኝት ላይ ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ትናንት ዕሁድ የሚያንማር ወታደራዊ አገዛዝ የሚፈጽመውን ጭቆና አውግዘው ቻይና እና የደቡብ እስያ ሀገሮች የሚያንማር ወታደራዊ ገዢዎች ዲሞክራሲን እንዲመልሱ እና ባለፈው ዐመት በተፈረመው የሰላም ውል የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ብሊንከን በታይላንድ ጉብኝታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶን ፕራሙድዊናይ ጋር የተገናኙ ሲሆን የስትራተጂያዊ አጋርነት መግለጫ ተፈራርመዋል።

XS
SM
MD
LG