በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሺንዞ አቤ ተገደሉ


የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ
የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ

ጃፓን ውስጥ በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው የሚታወቁት የሃገሪቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ዛሬ ዓርብ ማለዳ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል።

አቤን ለህልፈት ያበቃቸው ከኦሳካ በስተምሥራቅ በምትገኘው ናራ ከተማ ውስጥ አንድ የባቡር ጣቢያ ላይ ይካሄድ በነበረ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ንግግር እያደረጉ ሳሉ ደረታቸው ላይ በጥይት በመመታታቸው ነው።

አንድ መሣሪያ የያዘ ሰው ከኋላቸው ተጠግቶ ሁለት ጥይቶችን እንደተኮሰባቸው፣ ወዲያው እንደወደቁና ደም ይፈሳቸው እንደነበር በዘገባው ተመልክቷል።

ከምድር ወድቀው የነበሩትን አቤን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሊረዷቸው ይራኮቱ እንደነበር በማኅበራዊ መገናኛዎች የተለቀቁ የቪድዮ ምስሎች አሳይተዋል።

የ67 ዓመቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሆስፒታል ተወስደው አጣዳፊ ህክምና ቢደረግላቸውም ህይወታቸውን ማትረፍ አለመቻሉ ተዘግቧል።

በግድያው የተጠረጠረው ተሱያ ያማጋሚ የሚባል የ41 ዓመት ሰው በናራ ከተማ ፖሊስ መያዙን የጃፓኑ ዜና ማሠራጫ ኤንኤችኬ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG