በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከበርበራ ጋር ለተያያዙ መልዕክቶች ሬድዋን መልስ ሰጡ


ከበርበራ ጋር ለተያያዙ መልዕክቶች ሬድዋን መልስ ሰጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

ከበርበራ ጋር ለተያያዙ መልዕክቶች ሬድዋን መልስ ሰጡ

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በደረሱበት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ላይ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎችና አስተያየቶች “ያልጠበቅናቸው አይደሉም” ሲሉ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

መግለጫዎቹን በተለያየ መልክ እንደሚመለከቱ የጠቀሱት አምባሳደር ሬድዋን “በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ በልማቷ ከቀጠለችና ከዓለም አቀፍ መድረክ ጋር የሚያገናኛትን የባሕር በር ካገኘች በሁለት እግሯ ልትቆም ትችላለች የሚል ሥጋት አላቸው” ያሏቸው አካላት “እሳትና ነዳጅ ሲያቀብሉ አይተናል” ብለዋል።

በመጀመሪያ ደረጃ ኢትዮጵያ በልማቷ ከቀጠለችና ከዓለም አቀፍ መድረክ ጋር የሚያገናኛትን የባሕር በር ካገኘች በሁለት እግሯ ልትቆም ትችላለች የሚል ሥጋት አላቸው”

በሌላ በኩል “በቀጣናው ‘ተጨማሪ ውጥረት ሊፈጠር ይችላል’ በሚል ሥጋት ወደ ግጭት እንዳታመሩ የሚል ምክር የለገሱ፣ እንዲሁም ሁኔታውን በልኩ የሚገነዘቡና አዲስ ነገር እንደሌለ አይተው የተዉም አሉ” ሲሉ አክለዋል።

“የሆነው ነገር የገመትነው ቢሆንም የራሳችን የምንላቸው ሰዎች ከሌላው በለላይ ሲወራጩ ሲታይ ያስቆጫል፤ ያሳዝናልም” ያሉት ሬድዋን “ኢትዮጵያ ራሷ የምትቆጣጠረውና የምታለማው የባሕር በር መኖሩ ለሀገሪቱ ደኅንነትና የንግድ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም” አብራርተዋል።

በበርበራ ጉዳይ የሚመለከታቸው ወደ ዲፕሎማሲ እንዲገቡ ማሃማትና አሜሪካ መከሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:52 0:00

ለሶማሊላንድ ይሰጣል ስለተባለው ዕውቅናም የተናገሩት አምባሳደር ሬድዋን “የመግባቢያ ሰነዱ ጉዳይ ወደ ተሟላ ስምምነት ደርሶ መሬቱን ስንረከብና ሂደቱ ሲቋጭ እነሱ እውቅና ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት በተመለከተ ኢትዮጵያ አቋም የምትወስድበ ደረጃ ላይ እንደርሳለን የሚሉ አመላካች ነገሮች ናቸው ያሉት” ብለዋል።

“ስለዚህ ስምምነቱን አልተረከብንም፣ መስማማት እንዳለብን ግን ተስማምተናል፤ እርሱን ደግሞ በመግባቢያ ሰነድ ፈርመናል” ብለዋል።

በአነጋጋሪነቱ የሚሰጡ አስተያየቶችና መግለጫዎች የቀጠሉ ሲሆን የሶማሊላንድ ቅኝ ገዥ የነበረችው ብሪታንያም ውጥረቶች እንዲረግቡ ጠይቃለች።

የእንግሊዝ ኤምባሲ ከሞቃዲሾ ኤክስ ላይ ባወጣው መልዕክት “የሶማሊያን ፌደራል ሪፓብሊክ ሉዓላዊነትና የግዛት ጥብቅነት እንደምናከብር በድጋሚ እናረጋግጣለን” ብሏል።

/ዝርዝር ዘገባዎች ይቀጥላሉ/

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG