በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብራስልስ ፌዴራላዊ ዐቃብያነ-ህግ በሌሎች ሦስት ተጨማሪ ሰዎች ላይ ክስ መመስረታቸውን አስታወቁ


ፓላስ ደ ቦርስ (Place de la Bourse)በተባለ ቦታ በብራስልስ የጥቃት መታስብያ በሚደረግበት ወቅት ፖሊስ የቀኝ አክራሪዎች ተቃውሞ በከላከሉበት ወቅት የተነሳ ፎቶ እ.አ.አ.2016

የብራስልሱ ጥቃት 4 የUS ዜጎችን ጨምሮ ለ35 ሰዎች ሞት ሚክናት መሆኑ አይዘነጋም።

የብራስልስ ፌዴራላዊ ዐቃብያነ-ህግ ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ ካለፈው ሳምንት ጥቃት ጋር በተያያዘ፣ በሌሎች ሦስት ተጨማሪ ሰዎች ላይ ክስ መመስረታቸውን አስታወቁ።

የብራስልሱ ጥቃት 4 የUS ዜጎችን ጨምሮ ለ35 ሰዎች ሞት ሚክናት መሆኑ አይዘነጋም።

ሌላ 4ኛ ሰው በቁጥጥር ስር የዋለ እንደነበር፣ ዳሩ ግን በትናንቱ ዕለት መለቀቁን ከፌዴራሉ የዐቃቤ-ህግ ቢሮ የወጣው መግለጫ ጨምሮ አመልክቷል።

ክስ የተመሰረተባቸው ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ያሲን ያሲን ኤ. መሃመድ ቢ (Yassine A., Mohamed B) እና አቡበከር ኦ (Aboubaker O) መሆናቸው ከመገለጹ በስተቀረ፣ በጥቃቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ ይሁኑ/አይሁኑ፣ ከዐቃብያነ ህጉ ቢሮ የተሰጠ ዝርዝር የለም።

XS
SM
MD
LG