ዋሽንግተን ዲሲ —
"የዛሬው ቀን ለአገራችን የጨለማ ወቅት ነው" ያሉት የቤልጅግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቻርልስ ሚሸል (Charles Michel) ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁናቴ ነው፣ ሕዝባችን እንዲረጋጋና መንፈሰ-ጠንካራ እንዲሆን ጥሪ የማቀርበው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ዐቃቤ ህጉ ፍረዴሪክ ቫን ሊው አንደኛውን ፍንዳታ ያደረሰው አጥፍቶ-ጠፊ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ኩባን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የዩናትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማም ከሀቫና ባስተላለፉት መልዕክት፣ በደረሰው አደጋ ኃዘናቸውን ገልጸው፣ "እነዚህን የጥፋት መልዕክተኖች እገቡበት እየገባን ለፍርድ በማቅረብ፣ በዚህ እረገድ ለቤንጂግ ወዳጃችን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ብለዋል።
በዚሁ ጉዳይ አዲሱ አበበ ወደ ብራስልስ ደውሎ ሁለት ኢትዮጵያውያንን አነጋግሯል። አቶ ያሬድ ኃይለማራም እና አቶ ሰሎሞን መኩሪያ ይባላሉ። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።