በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብራስልስ ጸረ-ሽብር ዘመቻ ትምህርት ቤቶችና የባቡር ጣቢያዎች ተዘግተው ዋሉ


በብራስልስ ቤልጅም ከፍተኛ የጸረ-ሽብር ዘመቻ
በብራስልስ ቤልጅም ከፍተኛ የጸረ-ሽብር ዘመቻ

ብራስልስ ቤልጅም ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የባቡር ጣቢያዎች ዛሬ ማክሰኞ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ተገለጸ።

ብራስልስ ቤልጅም ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የባቡር ጣቢያዎች ዛሬ ማክሰኞ ዝግ ሆነው እንደሚውሉ ተገለጸ። እርምጃው፣ ባለሥልጣናት እአአ ባለፈው ኅዳር ፲፫ ቀን ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ቀንደኛ መሪ የሆነውን አሸባሪ ለማግኘት ፍለጋ ላይ በመሆናቸው ነው ተብሏል።

የቤልጅም ጠቅላይ ሚኒስትር ቻርልስ ሚሼል ትናንት ሰኞ ሲናገሩ፣ ጥቃት ለመፈጸም ሌላ ዛቻና ማስፈራሪያ በመኖሩ፣ ዋና ከተማዋ ቢያንስ እስከ ቀጣዩ ሳምንት ድረስ በለ የጥንቃቄ ደረጃ ውስጥ ትቆያለች ብለዋል።

አክለውም፣ አገሪቱ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ስላለባት፣ ነገ ረቡዕ ህፃናት ትምህርታቸውን፣ የባቡር አገልግሎቱም ሥራውን ይጀምራሉ ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ 130 ሰዎች በሞቱብ በፓሪሱ የሽብርተኞች ጥቃት ተጠርጣሪ የሆነው ሳልህ ኣብደሰላም (Saleh Abdeslam) ያለበትን በማግፈላለግ፣ የሞሮኮ ባለሥልጣት እገዛ እንዲያደርጉ በቤልጂግ መጠየቃቸውን አስታወቁ። የዜና ዘገባውን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

በብራስልስ ጸረ-ሽብር ዘመቻ ትምህርት ቤቶችና የባቡር ጣቢያዎች ተዘግተው ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:41 0:00
በብራስልስ ጸረ-ሽብር ዘመቻ ትምህርት ቤቶችና የባቡር ጣቢያዎች ተዘግተው ዋሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:47 0:00

XS
SM
MD
LG