በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመርዓዊ ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ


በመርዓዊ ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00

በመርዓዊ ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን ኢሰመኮ ገለጸ

የመርዓዊ ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል ሦስት ስፍራዎች፣ ባለፈው ጥር ወር በትንሹ 66 ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች እንደተገደሉ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል።

በመርዓዊው ጥቃት፣ “ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል” በሚል ከተገደሉት ቢያንስ 45 ሲቪሎች በተጨማሪ፣ “የፋኖ አባላት ናቸው” በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችም እንደተገደሉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችል የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዲሬክተር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ ጠቁመዋል፡፡ ከሌሎችም አካባቢዎች ለኮሚሽኑ በደረሱ የግድያ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደኾነ አክለው ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በበኩሉ፣ በመርዓዊው ጥቃት የተገደሉ ሲቪሎች ቁጥር ከ80 በላይ እንደሚኾን መግለጹ ይታወቃል፡፡ መግለጫውን ተከትሎም የአሜሪካ መንግሥት ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆ ነበር፡፡ ከመንግሥት በኩል ስለ ጉዳዩ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG