የፌደራል ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ ባለፈው ሳምንት ያደረጉትን ውጊያ ተከትሎ ከ50 በላይ ሲቪሎች በኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውን የከተማዋን ነዋሪዎች ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎችም ግድያው መፈፀሙንና የሟቾቹ አስክሬን በጅምላ መቀበሩን ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ነሐሴ ወር ላይ አውጥቶት በነበረው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ ወታደሮችና እና በፋኖ ሚሊሺያዎች መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት እና የፌደራል መንግሥት ቃል አቀባዮች፣ እንዲሁም የአማራ ክልል አስተዳደር፣ በመርዓዊ ከተማ ስለተፈጸመው ግድያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ እንዳልሰጡት ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል።
በአሜሪካ ድምፅ በኩል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ለመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳይ ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ ስልክ ላይ ደውለን አላገኘናቸውም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡
መድረክ / ፎረም