በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚቀርቡ ጥሪዎች ቢቀጥሉም፣ በአማራ ክልል ግጭቶች አይለው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በተለይም፣ በደቡብ ሜጫ ዞን መርዓዊ ከተማ እና በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በአዲስ ቅዳም እና በኮሶ በር ከተሞች ዳግም ያገረሹት ግጭቶች፣ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት መፍጠራቸውንና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማት፣ ዛሬ ማክሰኞ ለአራተኛ ቀን ዝግ ኾነው እንደዋሉ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።
በአዲስ ቅዳም እና በአካባቢው ካሉ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው የወጡ መኖራቸውንም አስተያየት ሰጭዎቹ አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ትላንት በፌስቡክ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ፣ በተለይ ከመርዓዊ እስከ ገርጨጭ ከተሞች ድረስ ባለው 23 ኪሎ ሜትር መንገድ ስምሪት ማድረጉን ጠቁሟል። የአማራ ክልል መንግሥትም ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ “የተጀመረው የሕግ የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤” ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም