ዋሺንግተን ዲሲ —
በአፍሪካ ቀንድ የመን ናይጄሪያና ደቡብ ሱዳን ብዛት ያለው ሰው ረሃብ የሚያልቅበት አደጋ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ዓለምቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው።
እአአ በ2011 አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ግማሽ በግማሽ አምስት ዓመት ያልሞላቸው ሕፃናት የሆኑ ከ2 መቶ ስልሣ ሺሕ በላይ ሰዎች የፈጀው ከባድ ረሃብ አሁን የዕርዳታ ድርጅቶችን ይዘገንናቸዋል፡፡
ሊሳ ሽላይን ከጄኔቫ ባስተላለፈችው ዘገባ እንደጠቆመችው ሰብዓዊ ቀውሱን ይበልጡን እያከፋው ያለው የገንዘብ ዕጥረት ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ