በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ"ቆሼ" ፍንዳታ ቤተሠቦቻቸውን ያጡ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ


በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በረጲ አካባቢ በተለምዶ “ቆሼ” የሚል ተቀጥያ ስም በተሰጠው ቦታ በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች ትላንት አደጋው የደረሰበትን አርባኛ ቀን አስበው ውለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በረጲ አካባቢ በተለምዶ “ቆሼ” የሚል ተቀጥያ ስም በተሰጠው ቦታ በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ቤተሰቦች ትላንት አደጋው የደረሰበትን አርባኛ ቀን አስበው ውለዋል፡፡

በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች፤ እንዲሁም ከክልል መንግሥታት የተዋጣ እርዳታ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ወይም ወደ 4 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ መድረሱ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተዘግቧል፡፡

በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ እንዲሁኔታው ቤት፣ ቦታ፣ ጥሬ ገንዘብ እንደሚሰጥም ተነግሯል፡፡

የአደጋው ሰላባ የሆኑ ሰዎች በሦስት ምድቦች እንደሚከፈሉ፤ እነርሱም ከዓመታት በፊት በአካባቢው ቤት ቀልሰው የሚኖሩ፣ በኪራይ ቤቶች የሚኖሩና የቆሻሻውን ክምር ሰርስረው ተጠልለው የሚኖሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በሕጋዊነት ቤት ሠርተው ለረጅም ዓመታት ከሚኖሩ፤ ቤቶቻቸው ከወደሙባቸውና ተከራይተው ከሚኖሩ ሁለት ሰዎችን ለጥያቄዎ መልስ ዝግጅት ጋብዘናል።

በነገራንች ላይ ይህ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት ሳይቀርብ የቀረው ከአድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጡ የመንግሥት ተጠሪ ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ አስተዳደር ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ መላሽ በማጣቱ ነበር፡፡

በዛሬውም ዝግጅት የከተማው አስተዳደር የኮምዩኒኬሽንስ ቢሮ ኃላፊን ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ብዙ ብንጥርም ስልካቸው ሰለማይነሳ የሚሉት ቢኖር ማካተት አልቻልንም፤ ስለመንግሥቱ ለመናገር ፍላጎት ያለው ወይም ዝግጁ የሆነ ማንም ባለሥልጣን ቢኖር ግን እኛም ለማስተናገድ ዝግጁ ነው፤ በጥረታችንም እንቀጥላለን፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በ"ቆሼ" ፍንዳታ ቤተሠቦቻቸውን ያጡ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG