በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቃድሾ ሶማሊያውያን በአዲሱ አስተዳደር ተስፋ አሳድረዋል


በሞቃድሾ ሶማሊያውያን በአዲሱ አስተዳደር ተስፋ አሳድረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00

በሞቃድሾ ሶማሊያውያን በአዲሱ አስተዳደር ተስፋ አሳድረዋል

ሶማሊያ አገሪቱን ወደ ግጭት ሊያመራ ከነበረውና፣ ለረጅም ጊዜ ካወዛገበው ምርጫ በኋላ፣ አዲስ ፕሬዚዳንት መርጣለች፡፡ የሶማሊያ ምክር ቤት፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሀሙድን፣ በቅፅል መጠሪያቸው “ፎርማጆ” ተብለው የሚታወቁትን፣ መሀመድ አቡዳልሂ መሀመድን እንዲተኩ መርጧቸዋል፡፡

መሀሙድ፣ የፕሬዚዳንትነቱን ሥልጣን የሚረከቡት፣ ከበርካታ አስቸጋሪ ፈተናዎች ጋር ሲሆን አገሪቱን ወደ ሰለምና እርቅ ለመምራት ቃል ገብተዋል፡፡

የሶማሊያው የ2022 ፕሬዚዳንታዊ፣ ምርጫ ወደ 39 ተፎካካሪዎችን ስቧል፡፡ 328 የህዝብ ተወካዮችና የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት ለሦስት ዙር ምርጫ ካደረጉ በኋላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሀመድ 214 ድምጽ አግኘተዋል፡፡

ይህ መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን ወይም ፎርማጆን ለመርታት በቂ በመሆኑ አሸናፊ ሆነው ወጥተዋል፡፡ መሀመድ ዳግመኛ ወደ ሥልጣን የተመለሱት እኤአ ከ2012 እስከ 2017 ድረስ አገሪቱን ከመሩ በኋላ ነበር፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባሰሙት ንግግር፣

“ልክ እኔ ቀደም ሲል ሥልጣኑን እንዳስረከቧቸው ሁሉ ተሰናባቹም ፕሬዚዳንት አሁን በማስረከባቸው ክብር ይገባቸዋል፣ የሶማሊያም ህዝብ እንዲሁ ተመሰሳሳይ መብትና አክብር አለው፡፡ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ የአላህ ሰላም በሁላችሁም ላይ ይሁን፡፡” ብለዋል፡፡

የሞቃድሾ ነዋሪዎች የወደፊቱ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ በምርጫው ውጤት ተደስተዋል፡፡

አዲሱ አስተዳደር ቁልፍ ችግር የሆነውን ሙስናን መዋጋትን ጨምሮ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት እንደሚኖሩት ባንድ ወቅት ሚኒስትር የነበሩት የቀድሞ ዲፕሎማት አብዱርሃማን ኑር መሀመድ ወይም በቅጽል ስማቸው ዲናሪ ተብለው የሚጠሩት፣ እንደሚከተለው አስረድተዋል፡፡

“ፕሬዚዳንቱ የሚታመኑና ኃላፊነት የሚሰማቸው መሪ መሆንን ጨምሮ ሙስናን መዋጋት ቅድሚያ ሊሰጧቸው ከሚገቧቸው ነገሮች መካከል አንዱ መሆን አለበት፡፡ አገሪቱ ከሙስና ነጻ መሆኗንን ለማረጋገጥ ለመላው የመንግሥት ኃላፊዎች በብቃትና በጎነታቸው አርአያ ሆነው ማገልገል ይኖርባቸዋል፡፡” የአዲሱ ፕሬዚዳንት ደጋፊዎቹ መሀሙድ ያላቸው ልምድ የሶማልያን ችግሮች ለማስወገድ ያግዛቸዋል ይላሉ፡፡

ሶማሊ ፒስ ላይን ተብሎ የሚጠራውና፣ መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት መስራች፣ አህመድ ዳኒ፣ በድጋሚ የተመረጡት አዲሱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት፣ ለሁለተኛ ጊዜ ያገኙትን እድል በሚገባ ይጠቀሙበታል ብለው ያምናሉ፡፡

ይህንንም ሲገልጹ “አዲሱ ፕሬዚዳንት አገሪቱን ቀደም ሲል ያስተዳደሯት መሆኑ ይጠቅማቸዋል፡፡ ስለዚህ የቱጋ እንደቆምንና የቱጋ እንደተሻሻልን ይገባቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡

በሞቃድሾ ጉዳናዎች፣ ሰዎች ስለ አዲሱ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አመራር ያላቸውን ጥሩ ተስፋ እየገለጹ ነው፡፡

የአገሪቱን ውጥንቅጥና ታሪክ በሚገባ የተረዱ አድርገውም ይመለከቷቸዋል፡፡

የሞድቃሾ ነዋሪ የሆኑት መሀመድ አህመድ፣

“ፕሬዚዳንቱ ሥልጣን ላይ በነበሩትበት እኤአ ከ2012 እስከ 2017 ድረስ የፌዴራል መንግሥት ተቋማትን ለማቋቋም ትላልቅ እምርጃዎችን በመወስዳቸው እስካሁን ትላልቅ ግቦችን አሳክተዋል፡፡ አሁን ቀሪዎቹን ሥራዎች እንደሚያጠናቅቁ እንተማመንባቸዋለን፣ ደግሞም እናምናቸዋለን፡፡” ብለዋል፡፡

መሀሙድ በርካታ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክቶችን ከደጋፊዎቻቸውና ከተለያዩ የዓለም መሪዎች ተቀብለዋል፡፡ ባሰሙት አጭር ንግግርም አገሪቱን አንድ ለማድረግ በሁሉም እርከን ካሉ የመንግሥት አካላት ጋር አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG