በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፓርላማ ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ መረጠ

የሶማሊያ ፓርላም ትናንት እሁድ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ውስጥ ባካሄደው ምርጫ የቀድሞው ሐሰን ሼኽ መሀሙድን በድጋሚ ሀገሪቱን እንዲመሩ መርጧቸዋል።
የሶማሊያ ፓርላም ትናንት እሁድ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ውስጥ ባካሄደው ምርጫ የቀድሞው ሐሰን ሼኽ መሀሙድን በድጋሚ ሀገሪቱን እንዲመሩ መርጧቸዋል።

የሶማሊያ ፓርላም ትናንት እሁድ በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ ውስጥ ባካሄደው ምርጫ የቀድሞው ሐሰን ሼኽ መሀሙድን በድጋሚ ሀገሪቱን እንዲመሩ መርጧቸዋል።

የምክር ቤት አባላቱ በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ ድንኳን ውስጥ በአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ከፍተኛ ጥበቃ ተሰብስበው በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ፕሬዚዳንቱን መርጠዋል።

ሠላሳ ስድስት ዕጩ ተፎካካሪዎች የቀረቡ ሲሆን የሁለቱም ምክር ቤቶች 327 አባላት በሦስት ዙር ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በመጨረሻው ዙር ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና ከሳቸው በፊት ፕሬዚዳንት የነበሩት ሀሰን ሼኽ መሀሙድ የተወዳደሩ ሲሆን ሀሰን ሼኽ መሀሙድ 214 ድምፅ ሲያገኙ መሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ 110 ድምፅ አግኝተው ተሸንፈዋል።

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አዲስ ተመራጩን ፕሬዚዳንት በሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቭዥን በቀጥታ ሥርጭት በተላለፈ ዝግጅት እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋቸዋል።

"አላህ ዛሬ ምሽት ምርጫችንን ለማጠናቀቅ ስላበቃን እናመሰግናለን፥ የመረጣችሁኝንም ያልመረጣችሁኝንም አመሰግናችኋለሁ፥ ወንድሜን አዲሱን ፕሬዚዳንት እንኳን ደህና መጡ እንኳን ደስ ያለዎ እላለሁ" ብለዋል።

አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ወዲያውኑ ቃለ መሃላቸውን የፈጸሙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌን የምርጫውን ሂደት ስለመሩ አመስግነዋቸዋል። መሀሙድ ባደረጉት አጭር ንግግር የፋርማጆን ደጋፊዎች አልቃወማቸውም የበቀል አድራጎት አይኖርም፣ ልዩነቶች ካሉን በሀገሪቱ ህግ መሰረት እንፈታቸዋለን" ብለዋል።

አዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት እአአ ከ2012 እስከ 2017 ድረስ ሀገሪቱን መምራታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG