በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራንን ፕሬዘዳንት የያዘችው ሄሊኮፍተር ተከሰከሰች


የኢራን ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ራኢሲ
የኢራን ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ራኢሲ

የኢራን ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ራኢሲ እና የሀገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የያዘች ሄሎኮፍተር በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ተራራማ አካባቢዎች ስትደርስ መከስከሷ ተገልጿል። በጉም በተሸፈነው የሀገሪቱ ክፍል ሰፊ የሆነ የነፍስ አድን ጥረት እየተደረገ ሲሆን ህዝቡ ጸሎት እንዲያደርግ ተጠይቋል።

አደጋው የተከሰተው በአያቶላህ አሊ ካሃመኔይ የስልጣን ተከታያቸው የሆኑት ኢብራሂም ራኢሲ ባለፈው ወር ላይ በእስራኤል ላይ የሚሳኤል ጥቃት በፈጸሙበት እና ኢራን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የዩራኒየም የጦር መሳሪያ ማበልጸጓን በቀጠለችበት ወቅት ነው።

በሌላ በኩል ኢራን በሺዓ እምነት ተከታዮች፣ ከሴቶች መብት ጋር በተያያዘ ጋር በተያያያዘ በተዳከመ ምጣኔ ሀብት እና ለዓመታት በዘለቀ ሕዝባዊ ተቃውሞ በገጠማት ወቅት መሆኑን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ይሄ ሁኔታ ለቴህራን አሳሳቢ ሲሆን የእስራኤል ሀማስ ጦርነትን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ሰፊ የሆነ ጦርነት እጣ ፈንታን የሚያቀጣጥል ሊሆን እንደሚችል አስግቷል።

ራይሲ በኢራን ምስራቅ አዘርባጃን ግዛት እየተጓዙ የነበረ ሲሆን፤ ከኢራን ዋና ከተማ ቴህራን በስተሰሜን ምዕራብ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰነው ጆልፋ በተባለች ከተማ አቅራቢያ ተጋጭተው ማረፋቸውን የሀገሪቱ የመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጿል። ተከትሎም የሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድጋሚ ሄሊኮፍተሩ የተጋጨው በኡዚ መንደር አቅራቢያ በምስራቅ በኩል ራቅ ባለ ስፍራ ነው ሲል የዘገበ ሲሆን የዜናው ዝርዝር እርስ በርሱ የሚጋጭ ሆኗል።

ከፕሬዘዳንት ራይሲ ጋር አብረው የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሂን፣ የኢራን የምስራቅ አዘርባጃን ግዛት ገዥ እና ሌሎች ባለስልጣናት እና ጠባቂዎች አብረው የነበሩ መሆናቸውን መንግሥታዊው የኢርና የዜና ወኪል ዘግቧል። አንድ የአካባቢው መንግሥት ባለሥልጣን የሄሊኮፍተሩን ሁኔታ “መከስከስ” ብለው ቢጠቅሱትም ሌሎች ግን “ተጋጭቶ ማረፍ” አሊያም “ክስተት” ሲሉ ገልጸውታል።

ሄሊኮፍተሩን ለማግኘት የነፍስ አድን ጥረት እየተደረገ ሲሆን፤ ሀገሪቱን በመመራት ላይ ያሉት በአያቶላህ አሊ ካሃመኔይ ህዝቡ ጸሎት እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG