እስራኤል ኢራን ውስጥ ዛሬ ዓርብ ሌሊት ባደረሰችው የአየር ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ እንዳልተሳተፈች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ተናግረዋል። እስራኤል ጥቃቱን ከማድረሷ ቀደም ብላ ዋሽንግተንን አሳውቃታለች በሚል የወጡ ሪፖርቶችንም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ለማረጋገጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ያያችሁትን ሪፖርት በሚመለከት የምለው ነገር የለም፥ ዩናይትድ ስቴትስ በአንድም ጥቃት አለመሳተፏን ግን እነግራችኋለሁ"
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጣሊያን ካፕሪ ላይ ከቡድን 7 አባል ሀገሮች የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ በኋላ በተካሄደ ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ሲናገሩ "ያያችሁትን ሪፖርት በሚመለከት የምለው ነገር የለም፥ ዩናይትድ ስቴትስ በአንድም ጥቃት አለመሳተፏን ግን እነግራችኋለሁ" ማለታቸው ተዘግቧል።
የቡድን 7 ሚኒስትሮች ስብሰባ ግጭቶቹ በቀጣናው እንዳይስፋፉ ለመከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ መወያየቱን ብሊንከን ተናግረዋል።
ስብሰባውን የመሩት የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒዮ ታጃኒ እስራኤል ጥቃቱን በሚመለከት "በመጨረሻ ደቂቃ" አሳውቃት እንደነበረ ዩናይትድ ስቴትስ ለቡድን ሰባት አጋሮቿ መግለጿን አመልክተዋል።
የቡድን-7 ሚኒስትሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ ኢራን እስራኤል ላይ ባደረሰችው ጥቃት ምክንያት አዲስ እቀባ እንደሚጣልባት አስታውቀው ፍጥጫ እንዲረግብ አሳስበዋል። ቴህራን ለጊዜው ማሳሰቢያውን የተቀበለች ይመስላል ተብሏል።
መድረክ / ፎረም