በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደሳለኝ ጫኔ ከእስር ተለቀቁ

ከግራ ወደ ቀኝ የምክር ቤት አባልና የአብን አባል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፣ አብዲ ኢሌ በሚለው ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ዑመር እና የሜቴክ የቀድሞ ዳይሬክተርበሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ።
ከግራ ወደ ቀኝ የምክር ቤት አባልና የአብን አባል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ፣ አብዲ ኢሌ በሚለው ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ዑመር እና የሜቴክ የቀድሞ ዳይሬክተርበሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ።

- የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የአብዲ ኢሌ ክስ ተቋረጠ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደራሴና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ ከእስር መለቀቃቸውን ጠበቃቸው አስታወቁ። ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ነበር በፖሊስ ተወስደው በእስር ላይ የከረሙት፡፡

በሌላ ዜና በቀድሞ የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እና ኢነጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዲሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና አብዲ ኢሌ በሚለው ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ዑመር ክስ መቋረጡን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ፍትሕ ሚኒስቴር ለሕዝብ ጥቅም ሲል ክሶቹ እንዲቋረጡ መወሰኑን መገናኛ ብዙሃኑ አክለው ጠቅሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG