በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ


አቶ አብዲ ሞሐመድ ኦማር
አቶ አብዲ ሞሐመድ ኦማር

አብዲ ኢሌ በሚለው ቅፅል ስማቸው የሚታወቁት የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።

አቶ አብዲ መሐመድ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ አትላስ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መያዛቸውም ታውቋል።

ዐቃቤ ሕግ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ያዋለበትን የወንጀል ድርጊት ለሀገር ውስጥ መገናና ብዙሃን ሲዘረዝር ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በብሔር ግጭት ቀስቃሽነት፣ በኃይማኖት መካከል ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል የሚል ነው።
የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመርና የሌሎች ስድስት የምክር ቤቱ አባላትና የክልሉ ባለሥልጣናት ያለመከሰስ መብት ማንሳቱ ይታወሳል።

(የዚህን ዜና ዝርዝር በምሽቱ ፕሮግራማችን ይጠብቁ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG