በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ አለመግባባት የጎላበት የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ


የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ አለመግባባት የጎላበት የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ አለመግባባት የጎላበት የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ተጠናቀቀ

የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ፣ ትላንት እሑድ ሌሊት ላይ በተደረገ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል፡፡

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ፣ ጉባኤው በተጀመረበት ቅዳሜ ዕለት፣ “የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ከሆቴል እንዳልወጣና ጉባኤው ወደሚካሔድበት የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ቅጽር እንዳልገባ ሙከራ አድርገዋል፤” ሲሉ ከሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ክሱን ያስተባበለ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱ ከተለመደው ዓለም አቀፍ አሠራር ውጭ ለመሆን መሞከራቸውን አስታውቋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ፣ በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ፣ “ኢትዮጵያ የግዛታችንን አካል ወደ ራሷ ለማጠቃለል ያደረገችው ነው፤” ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሶማሊያን የመጉዳት ዓላማ እንደሌላት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው፣ የመግባቢያ ሰነዱን ተከትሎ የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ፣ ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ጋራ ፊት ለፊት ተገናኝተው ለመወያየት ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት፣ ይህን ጨምሮ በአጠቃላይ የሶማሊያ ጉዳይ ላይ ዛሬ ተወያይቷል። የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት አባላት በሶማሊያ ጉዳይ ላይ የቀረበውን ማብራሪያ አዳምጠዋል።

ማብራሪያውን ከሰጡት አንዷ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሶማሊያ ልዩ ተወካይ ካትሪዎና ሌይንግ ሲሆኑ ካነሷቸው ጉዳዬች አንዱም በሞቃዲሾና በአዲስ አበባ መካከል የሚታየው ውጥረት ነው።

“በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ሶማሊያ ውስጥ የፈጠረው ስሜት የአገሪቱ መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ጫና እያሳደረ መሆኑን እንገነዘባለን” ያሉት ልዩ ተወካይዋ ፕሬዚዳንቱ በምላሻቸው ቁጥብ እንዲሆኑ እናበረታታሃለን በማለትም አክለዋል። ሁሉም ወገኖች ገንቢ ወደሆነ ውይይት እንዲገቡም ጥሪ አቅርበዋል።

አልሻባብ ሁኔታው አባላትን ለመመልመል እየተጠቀመበት መሆኑም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ከማርገብ አንጻር፣ “ትናንት በተጠናቀቀው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ትርጉም ያለው ዕመርታ አለመታየቱም አሳዛኝ ነው” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG