በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ “ራስን በማስራብ አምልኮ” የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ300 በላይ ደረሰ

በኬንያ፣ የቤተ ክርስቲያን መሪያቸውን “የረኀብ አምልኮ ትዕዛዝ” ተቀብለው ከምግብ በመታቀብ ራሳቸውን በማስራባቸው፣ ለኅልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ300 ማለፉን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ይህ የተገለጸው፣ ባለሥልጣናት፥ ተጨማሪ አስከሬኖችን ከጫካ ውስጥ አግኝተው እንዳወጡ ከተነገረ በኋላ ነው፡፡በቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ፣ ከአምልኮ ጋራ ተያይዘው ከደረሱ አሳዛኝ አደጋዎች፣ ይህ አስከፊው እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ በሻካሆላ ጫካ ውስጥ 19 አስከሬኖች ተቀብረው ከተገኙ በኋላ እስከ አሁን ባለው መረጃ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 303 ደርሷል። ከ600 በላይ የሚኾኑቱ ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም፡፡

“ራሳችኹን በማስራብ ብትሞቱ የዓለም ፍፃሜ ከመድረሱ በፊት ኢየሱስ ክርስቶስን ታገኙታላችኹ፤” በሚል፣ ሟቾችን አነሣስተዋል የተባሉ የመልካም ዜና ዐለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን መሪው ፖል ማኬንዚ ኢንቴንጌ ፣ ባለፈው ሚያዝያ እጃቸውን ለፖሊስ ሰጥተዋል፡፡ ማኬንዜ፣ የዋስትና መብት ተከልክለው በእስር እንደሚገኙም ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG