በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ የሃይማኖት መሪያቸውን ተከትለው ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 73 ደረሰ

ኬንያ ውስጥ የሃይማኖት መሪያቸውን ተከትለው ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 73 ደረሰ
ኬንያ ውስጥ የሃይማኖት መሪያቸውን ተከትለው ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 73 ደረሰ

ኬንያ ውስጥ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የቤተ ክርስቲያኑ መሪያቸው ያሏቸውን ተቀብለው በመጾም በረሃብ የሞቱ ሌሎች ሰዎች ይኖራሉ የሚለው ሥጋት ጨምሯል። በርካታ አስከሬኖች በጅምላ መቃብር ውስጥ ተቀብረው ያገኙት ፖሊሶች አሁንም ፍለጋውን ቀጥለዋል።

በጾም ራሳቸውን አስርበው የሞቱት አማኞች ቁጥር 73 መድረሱን ትናንት ማታ ፖሊስ አስታውቋል። በህይወት የተገኙ በርካቶች ወደሀኪም ቤት ተወስደዋል።

ምዕመናኑን ጾማችሁ ብትሞቱ ኢየሱስ ክርስቶስን ታገኙታላችሁ ያሏቸው የቤተ ክርስቲያኑ መሪ ፖል ማኬንዜ ኒቴንጌ ሲሆኑ ፖሊሶች በደረሳቸው ጥቆማ ማሊንዲ ከተማ አቅራቢያ ጫካ ውስጥ ያለውን መሬታቸው ወርረው ሰለባዎቹን ሲፈልጉ ቆይተዋል።

ዜናው መላ ሀገሪቱ ያስሽበረ ሲሆን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ "ተገቢ ያልሆነ የሃይማኖት እንቅስቃሴ የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ዕርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የሞቱት ሰዎች ቁጥር ይጨመራል የሚል ሥጋት አለ።

XS
SM
MD
LG