በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ውስጥ ራሳቸውን በጾም አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 90 ደረሰ


ኬንያ ውስጥ የቤተ ክርስቲያናቸውን መሪ ያሏቸውን ተከትለው በመጾም ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 90 መድረሱ ተገለጠ፡፡
ኬንያ ውስጥ የቤተ ክርስቲያናቸውን መሪ ያሏቸውን ተከትለው በመጾም ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 90 መድረሱ ተገለጠ፡፡

ኬንያ ውስጥ የቤተ ክርስቲያናቸውን መሪ ያሏቸውን ተከትለው በመጾም ራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 90 መድረሱ ተገለጠ፡፡ ብዙ ህጻናት እንዳሉባቸው ተጠቁሟል፡፡ ፖሊስ የአስከሬን ማሳረፊያዎች ስለሞሉ የሰለባዎች ፍለጋ ሥራውን ማቋረጡን አስታውቋል፡፡

የባህር ዳርቻዋ ማሊንዲ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ሻንኮሌ ደን ውስጥ የጅምላ መቃብር መገኘቱ በሀገሪቱ ህዝብ ዘንድ ትናንት መርማሪዎች 17 አስከሬኖች ማግኘታቸውን ተከትሎም ሌሎችም በዚሁ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ይኖራሉ የሚለውን ስጋት ቀስቅሷል፡፡

የኬንያ መንግሥት ጽንፍ የያዘ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የሚያካሂዱ አካላት ላይ ዕርምጃ እንወስዳለን ሲል አስጠንቅቋል፡

XS
SM
MD
LG