በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማዕከላዊ ጎንደር በተፈጸመ ጥቃት ኹለት የቀይ መስቀል ሠራተኞች መጎዳታቸው ተገለጸ


በማዕከላዊ ጎንደር በተፈጸመ ጥቃት ኹለት የቀይ መስቀል ሠራተኞች መጎዳታቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:27 0:00

በማዕከላዊ ጎንደር በተፈጸመ ጥቃት ኹለት የቀይ መስቀል ሠራተኞች መጎዳታቸው ተገለጸ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ ወረዳ፣ ኹለት ሠራተኞቹ በሥራ ላይ እያሉ በተፈጸመባቸው ጥቃት መጎዳታቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስታወቀ።

የማኅበሩ የኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ አቶ መስፍን ደረጀ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞች በሕክምና ላይ መኾናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚያው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አካባቢ ደግሞ፣ መንግሥት የልዩ ኃይል አባላትን ወደ ሌሎች የጸጥታ ተቋማት ለማካተት ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም በተቀሰቀሰው ሁከት፣ ኹለት የካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት ሠራተኞች መገደላቸውን የርዳታ ድርጅቱ መግለጹ ይታወሳል።

ስለተፈጸሙት ጥቃቶች ከመንግሥት አካል አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/


XS
SM
MD
LG