በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የፍልስጤም ታጣቂዎች በዌስት ባንክ በእስራኤል ወታደሮች ተገደሉ


የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ ናቡለስ ከተማ
የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ ናቡለስ ከተማ

ናቡለስ በተሰኘው ሰሜናዊ ዌስት ባንክ አካባቢ የሚገኙ ወታደሮች ላይ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ፤ ሦስት የፍልስጤም ታጣቂዎች መገደላቸውን የእስራኤል ሰራዊት አስታወቀ። በቀጠናው ግጭት ቀጥሏል።

ሰራዊቱ ባወጣው መግለጫም “ሦስት ታጣቂዎች በተኩስ ልውውጡ ሲገደሉ አንድ ተጨማሪ አንድ ታጣቂ ደግሞ እጅ ሰጥቶ ተይዟል” ሲል አስታውቋል።

አዲሱ የጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት ከጀመረ አንስቶም የእስራኤል እና ፍልስጤም ጦርነት፤ የ81 ፍልስጤማዊያን ጎልማሶች፣ እና ህጻናትን ህይወት የነጠቀ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ታጣቂዎች እና ሲቪሎች ይገኙበታል።

ኤኤፍፒ ከሁለቱም አካላት አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረትም 12 እስራኤላዊያን ሲቪሎች፣ ሦስት ህጻናት፣ አንድ ፖሊስ እና አንድ ዩክሬናዊ ሲቪልተገድለዋል።

XS
SM
MD
LG