በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፎች በቀጠሉበት የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ወደ እስራኤል አቀኑ


የተቃውሞ ሰልፎች በቀጠሉበት የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ወደ እስራኤል አቀኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:28 0:00

የተቃውሞ ሰልፎች በቀጠሉበት የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ወደ እስራኤል አቀኑ

የዩናይትድ ስቴትሱ መከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ዛሬ ሃሙስ እስራኤል ገብተዋል። የጉዟቸውም ዓላማ በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ የሚታየው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱ አጋር አገሮችን ኢራን የምትፈጽመውን ለመቃወም ከሚያደርጉት ጥረት ሊያደናቅፋቸው እንደሚችል አገራቸው ያደረባትን ሥጋት ለማስተላለፍ መሆኑ ታውቋል።

በአካባቢው አገሮች ጉብኝት ላይ የሚገኙት ኦስቲን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፡ የሃገሪቱን የሕግ ሥርዓት ለመቀየር የያዙትን ዕቅድ ለመቃወም እየተካሄዱ ያሉት የጎዳና ላይ ሰልፎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ተከትሎ ነው፤ በጥድፊያ ቀጣዩን የጉዟቸው መዳረሻ በመቀየር ወደዚያ ያቀኑት።

ይህ በእንዲህ እንዳልለ፡ ከሰዓታት ቀደም ብሎ የእስራኤል ኃይሎች በዌስት ባንክ ሶስት እስላማዊ ታጣቂዎችን መግደላቸው ተዘግቧል።

ነገሮች እየተካረሩ እና እየተወሳሰቡ በመጡበት ባሁኑ ወቅት፤ በጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የፔንታጎን ባለሥልጣን “መከላከያ ሚንስትር ኦስቲን ስለ ሁለቱም ጉዳዮች፣ (ዌስት ባንክ እና ኢራን) አመርቂ ውይይቶችን ለማድረግ ፍጹም ብቁ የሆነ ችሎታ አላቸው።” ሲሉ፡ የመከላከያ ሚንስትሩን ጉዞ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት አመልክተዋል።

ይሁንና እስራኤል የዌስት ባንክን በተመለከተ ያላት አቋም "አሁን ስትራተጂያዊ ነው በሚባለው ስጋት ላይ ትኩረት የማድረግ አቅማችንን ይጎዳዋል። ይህም የኢራን የኒውክሌር ማበልጽግ አደገኛ ግስጋሴ እና ያልተቋረጠው በክልል እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታይ የጠብ አጫሪነት ዝንባሌ ነው።" ብለዋል ባለሥልጣኑ።

መከላከያ ሚንስትር ኦስቲን ከBEN GURION AIRPORT አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ በእስራኤሉ አቻቸው የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ ከሚንስትር ጋላንት እና ከጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ጋር በአቅራቢያው ከሚገኝ የኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተነጋግረዋል። ኦስቲን ቀደም ሲል ትናንት ማምሻው ላይ ገብተው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ከሚገኝባት ቴል አቪቭ ሊያድሩ ነበር የታቀደው። ሆኖም ፀረ ኔታንያሁ ተቃውሞዎቹ የትራፊክ መስተጓጎል ይፈጥራሉ በሚል ሥጋት ያ እቅድ ኋላ ላይ ሊቀየር ችሏል።

"ኦስቲን ለእስራኤል ደህንነት መረጋገጥ ላይ ቁርጠኛ ናቸው። ሆኖም ተባብረን ለመስራት እና ግንኙነታችንን ለማጠናከር የቻልንባቸው ዋነኛ መንገዶች፡ ተመሳሳይ እሴቶችን የምንጋራ ዲሞክራሲያዊ መንግስታት በመሆናችን ነው።” ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን፣ “እነኛም እሴቶች፡ የመቃወም መብትን ይጨምራሉ።” ሲሉ አክለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG