የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ ዛሬ ባደረገው የቀን አሰሳ 10 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 102 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በቀን በተፈጸመውና ፍልስጤማውያንን ለመያዝ በተካሄደው አሰሳ አንድ የ72 ዓመት አዛውንትም ከሟቾቹ አንዱ መሆናቸውን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
አሰሳው የተደረገው ተደጋጋሚ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በሚታይባት ናብለስ በተሰኘችው ከተማ ሲሆን፣ የእስራኤል ሰራዊት ስለ አሰሳው ማረጋገጫ ቢሰጥም ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥቧል፡፡
በዌስት ባንካና ምሥራቅ እየሩሳሌም በዚህ ዓመት ከታዩት ሁከቶች ከፍተኛ ሞት የተመዘገበበት ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ከ50 በላይ የሚሆኑ ፍልስጤማውያን በእስራኤል በተያዘችው ዌስት ባንክና ምሥራቅ እየሩሳሌም መገደላቸው ታውቋል።