ጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው። በጡት ካንሰር ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች በዓለም ላይ ከ100 ወንዶች አንዱ፤ በሴቶች ላይ ደግሞ ከአራት ሴቶች መሃከል አንዷ የጡት ካንሰር ሊኖርባት እንድሚችል አመላክተዋል። ይህም የጡት ካንሰር በዓለም ላይ ቀዳሚ የሴቶች ህይወት የሚያልፍበት በሽታ እንዲሆን አድርጎታል።
በተጨማሪም በሽታውን ለመከላከል የሚሰሩ ምርምሮች ጥቁሮችን አካታች ባለመሆናቸው ይበልጡን ጥቁር ሴቶች በበሽታው እንደሚጠቁ ጥናቶች ያመላክታሉ።