በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የህጻናት ካንሰር ህሙማንን እና የወላጆቻቸውን ጭንቀት የተሸከመው ተቋም


የህጻናት ካንሰር ህሙማንን እና የወላጆቻቸውን ጭንቀት የተሸከመው ተቋም 
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00

የህጻናት ካንሰር ህሙማንን እና የወላጆቻቸውን ጭንቀት የተሸከመው ተቋም 

ኢትዮጵያ ውስጥ እ.ኤ.አ በ2015 ዓ.ም ከሆስፒታሎች በተወሰደ መረጃ መሰረት በአመት 150,000 የካንሰር ህሙማን የሚመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 6000 ያህሉ ሕጻናት መሆናቸውን ቢ ኤም ሲ ካንሰር የተሰኘ የሕክምና መጽሄት (ጆርናል) ዘግቧል፡፡ ይሁንና የሕጻናት ካንሰር ምርመራ ለመከታተል ወደ ትላልቅ ከተሞች ከልጆቻቸው ጋር የሚመጡ ወላጆች በትራንስፖርት፣ በምግብ፣ በማረፊያ እና በመድሃኒት ግዢ ወጪዎች የተነሳ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ፡፡

ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ በሆነ ተግዳሮትን ያሳለፉ ወላጆች የካንሰር ህሙማን ሕጻናትን እና የወላጆቻቸውን ችግር ለመቅረፍ ተስፋ አዲስ የወላጆች እና የህጻናት ካንሰር ህሙማን ማረፊያ በተለያዩ የህጻናት ህክምና በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ ማዕከል ሊከፍቱ ችለዋል፡፡ ወላጆቹ ባደረጉት በጎ ፍቃድ እና ተነሳሽነት ከሌሎች አለም አቀፍ የግብረ ሰናይ ተቋማትም ጋር ሊተባበሩ ችለዋል፡፡

ሕጻናት በተቋሙ ማረፊያ፣ የመጓጓዣ፣ የትምህርት፣ የልደት ክብረ በዓል ስነስርዓት፣ የልብስ እና የሌሎች ድጋፎች የሚደረግላቸው ሲሆን ከሆስፒታሎች ውጭ የሚደረጉ የህክምና ወጪዎችም በማዕከሉ ይሸፈናሉ፡፡ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም እና ልጃቸውን ማዕከሉ ውስጥ በማረፍ የሚያስታምሙት ወ/ሮ ኬሪያ መሃመድ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ)

XS
SM
MD
LG