በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኔቶ አባል ሀገሮች የመሪዎች ጉባዔ ተጠናቀቀ


ስፔን ማድሪድ ላይ የተሰባሰቡት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች ዛሬ ጉባዔ ተጠናቀቀ።
ስፔን ማድሪድ ላይ የተሰባሰቡት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች ዛሬ ጉባዔ ተጠናቀቀ።

ስፔን ማድሪድ ላይ የተሰባሰቡት የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) መሪዎች ዛሬ ጉባዔቸውን ዛሬ አጠናቅቀዋል። በመሪዎቹ ጉባዔ ለድርጅቱ የተቀረጸውን አዲስ የስትራተጂ መርኃ አጽድቀዋል። በዚህም የሩሲያ ወራሪነት እና ቻይና የደቀነችው ጥልቅ ፈተና እንዲሁም በሁለቱ ሀገሮች መካከል እየተጠናከረ የመጣው ስትራቴጂያዊ ሽርክና ህብረቱ ቅድሚያ ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል እንደሚሆን ተመልክቷል።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋመው የምዕራብ ሀገሮች ወታደራዊ ቃል ኪዳን ድርጅት ሩስያን "በግንባር ቀደምነት ቀጥታ ሥጋት የደቀነች ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ ገልጿታል። ይህም ብቻ ሳይሆን ቻይና የኔቶ አባል ሀገሮችን ጸጥታ፣ ጥቅሞች እና እሴቶች እየተፈታተነች ትገኛለች ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷታል።

መሪዎቹ ከዚህም በተጨማሪ ዩክሬን አምስት ወራት ያስቆጠረውን የሩስያ ወረራ ለመመከት ለምታደርገው ጥረት ድጋፍ መስጠታችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዩናይትድ ስቴትስ አውሮፓ ውስጥ ያላትን ወታደራዊ አቅም እንደምታጠናክር ትናንት አስታውቀዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬቼፕ ታይፕ ኤርዶዋን ስዊድንና ፊንላንድ ህብረቱን መቀላቀል ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ በማንሳታቸው ፕሬዚዳንት ባይደን አመስግነዋቸዋል።

XS
SM
MD
LG