በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስፔን ኔቶ በአፍሪካ ያለው የሩሲያ መስፋፋት ጉዳይ እንዲያይ ግፊት እያደረገች ነው


በማድሪድ ስፔን በመጪው ሳምንት ከሚሄደው ከኔቶ አባል ሃገራት ስብሰባ በፊት በቅኝት ላይ ያለ ፖሊስ
በማድሪድ ስፔን በመጪው ሳምንት ከሚሄደው ከኔቶ አባል ሃገራት ስብሰባ በፊት በቅኝት ላይ ያለ ፖሊስ

የሩሲያ ዩክሬንን መውረር መጪውን በማድሪድ የሚካሄደውን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ሃገራት ኔቶ ስብሰባ ትኩረት እንደሚሆን ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ስፔን እና የሌሎች አባል ሃገራቱ ምዕራባዊያን ሕብረት ብላድሚር ፑቲን በአፍሪካ ላይ የሞስኮን መስፋፋት ለማስረጽ ቅጥር ተዋጊዎችን የሚያቀርቡበት ሁኔታ እንዲታይ ጫና እያደረጉ ነው።

ከመጪው ማክሰኞ እስከ ሃሙስ ድረስ ለሶስት ቀናት በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ስፔን በአውሮፓ ደቡባዊ ክፍል በአፍሪካ ስላለው ሁኔታ የጸጥታ ሰነዶችን እንዲዘጋጁ ኔቶን እየገፋች ትገኛለች።

ስፔን ከብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ እና ጣሊያን ጋር በመሆን ፕሬዘዳንት ፑቲን በአፍሪካ ላይ እያሳደሩት ያለውን ጫና እና የቻይና መስፋፋት ትኩረት እንዲደረግበት ግፊት የምታደርገው።

ክሬምሊን ከዋግነር ቅጥር ተዋጊዎች ቡድን ጋር ምንም ዓይነት ትስስር እንደሌለው ሲያስታውቁ ቆይተዋል። ከሰሞኑ በሚካሄደው የኔቶ ስብሰባ ላይ ለእስያ ፓስፊክ ሃገራት ያላቸውን ትኩረት ለማሳየት የጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ አውስትሬሊያ እና ኒውዝላንድ ሃገራት መሪዎችን የተጋበዙ ሲሆን ከአፍሪካም የሞሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃገራቱ በሚያደርጉት የመሪዎች የእራት ግብዣ ላይ ለመወያየት ተጋብዘዋል።

ኔቶ በመጪው ስብሰባው በምዕራባዊ ሳሃራ አልጄሪያ፣ ማሊ እና ሴኔጋል ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩም አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG