ሱዳን ጎረቤቷ የሆነችው ኢትዮጵያ 7 የተማረኩ ወታደሮችንና አንድ ሲቪል ገድላብኛለች ስትል ከሳ፣ “የፈሪ ሥራ” ብላ ለጠራቸው እርምጃም አጸፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
ኢትዮጵያ በበኩሏ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባወጣችው መግለጫ በድንበር አካባቢ በሱዳን ሰራዊትና በኢትዮጵያ ወገን ባሉ ሚሊሺያዎች መካከል በተነሳ ግጭት የሰዎች ህይወት በመቀጠፉ ሐዘኗን ገልጻ ምርመራ እንደምታካሂድ አስታውቃለች። “ክስተቱም የሱዳን ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው በመግባታቸው ምክንያት የተፈጠረ ነው” ስትል ኢትዮጵያ በመግለጫው አክላለች።
ክስተቱን ተከትሎ ሱዳን ቢትዮጵያ የሚገኘውን አምባሳደሯን “ለምክክር” በሚል ወደ ካርቱም እንደምትጠራ አስታውቃለች።
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስና አሶስዪትድ ፕሬስ የላኩትን ሪፖርት እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ያወጣውን መግለጫ ይዘት እንግዱ ወልዴ አዘጋጅቶታል።