በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድንበር ላይ ባለው ሁኔታ የሱዳን፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና የህወሓት መግለጫዎች


ኢትዮ - ሱዳን ካርታ
ኢትዮ - ሱዳን ካርታ

“ኢትዮጵያ የተማረኩ ሰባት ወታደሮችንና አንድ ሲቪል ገድላብኛለች” ሲል የሱዳን ጦር ትናንት ያሰማውን ክስ “ወታደሮቻችን በአካባቢው አልነበሩም” ሲል የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስተባብሏል።

የተፈጠረውን ሁኔታም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ “አሳዛኝ” ብሎታል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣

“የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ ገብቷል” ያሉት የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሽያ ጋር መጋጨቱን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የሱዳን ታጣቂዎች በአብድራፊና በምዕራብ አርማጭሆ በኩል ከትናንት ጠዋት ጀምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እንደከፈቱ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አስተዳዳሪ ቢሰጥ ወርቁ ባለፈው ሳምንት በነበረው ግጭት ከሁለቱም ወገን ህይወት መጥፋቱን ገልፀዋል።

ከተገደሉት መካከል ከሱዳናዊያኑ ጋር አብረው ተሰልፈዋል ያሏቸውንና የህወሓት ታጣቂዎች እንደሆኑ የጠቆሟቸው መኖራቸውን ቢናገሩም ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ውንጀላውን በብርቱ አስተባብሏል።

/ዝርዝሩን ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:18 0:00

XS
SM
MD
LG