በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጭስ ቦንብ አፈንድቷል የተባለው ተጠርጣሪ ለተጨማሪ ምርመራ ተቀጠረ


የጭስ ቦንብ አፈንድቷል የተባለው ተጠርጣሪ ለተጨማሪ ምርመራ ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:07 0:00

የጭስ ቦንብ አፈንድቷል የተባለው ተጠርጣሪ ለተጨማሪ ምርመራ ተቀጠረ

በኢድ አልፈጥር በዓል ላይ የጭስ ቦንብ አፈንድቷል በሚል ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል አድማ ብተና አባል ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ላይ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት።

ጉዳዩን ለማየት ዛሬ ተሰይሞ የነበረው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ 2ኛጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ምን እንዳከናወነ ያቀረበውን ሪፖርት አዳምጧል።

ፖሊስ የተጠርጣሪው ቃል መቀበሉን፣ ለተጠርጣሪው የገንዘብ ድጋፍ መኖርና አለመኖሩን ለማጣራት ለ18 ባንኮች ደብዳቤ መላኩን ፣እንዲሁም የግል ስልኩ ላይምርመራ እንዲደረግ ለብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አግልግሎት ደብዳቤ ልከው ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አስረድቷል።

በተጨማሪም የስልክ ቁጥሩ በማንስም እንደወጣ ለማጣራት ኢትዮ ቴሌኮምን በደብዳቤ መጠየቁን በተጨማሪም የፈነዳውን አስለቃሽ ጭስ ቦንብ ፍንጣሪ በፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግ መላኩን እኛ አንድ የምስክር ቃል መቀበሉን ለችሎቱ አስረድተዋል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ ለምርመራው በተሰጠ የጊዜ ገደብውስጥ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ከሻንጣው ጀምሮ ብርበራ መደረጉን እና ምንም ነገር እንዳልተገኘበት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

“በድንገት ያጋጠመ ነገር እንጂ ሆን ብዬ ያደረኩት አይደለም፤ ምንም ወንጀል አልሰራሁም ከታሰርኩበት ጊዜ ጀምሮ ጠያቂ የለኝም፤ አንድ ሳምንት በር ተዘግቶብኝ ታስሬ ነበር" ሲል ለችሎቱ አቤቱታ አቅርቧል።

የችሎቱ ዳኛ አሁን ስላለሁ ሁኔታ ባቀረቡት የማጣሪያ ጥያቄም፤ በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች እስረኞች ጋር መቀላቀሉን ገልጿል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠረጣሪውን በተመለከተ እያከናወነ ላለው ምርመራተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ 10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቅዶለታል።

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ይቀሩኛል ብሎ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበትን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ስጥቷል።

XS
SM
MD
LG