አዲሱ ዓመት የአካዳሚ ሽልማት “ኦስካር” ምርጫዎችም መጀመሪያ ነው።
መጽሀፍ ደራሲው ዳን ሀርሊ ለአራት አሰርት ዓመታት ያህል መንገድ ላይ ስለሚያገኛቸው የኒው ዮርክ ነዋሪዎች የ60 ሴኮንድ ርዝማኔ ያላቸው ታሪኮች ሲጽፍ ኖሯል። ነገር ግን አላፊ አግዳሚውን በሥነ ጽሁፍ ችሎታው ከማስደነቅ ባለፈ፣ ሀርሊ እስከመሸለም የበቃ የሳይንስ ፀኃፊ ነው። አና ኔልሰን፣ ሀርሊን በኒው ዮርክ መንገዶች ላይ አግኝታዋለች። የአና ኔልሰንን ትረካ ግርማ ደገፋ ያቀርበዋል።