አስራ አራተኛው የቅዱስ ያሬድ እና ግዕዝ ቋንቋ ጉባዔ ባለፈው ሳምንት በአክሱም ተካሂዷል። ለአራት ቀናት በቆየው መርኃግብር ምሁራን በቅዱስ ያሬድ እና ግዕዝ ቋንቋ ላይ ትኩረት ያደረጉ በሳይንሳዊ ምርምሮችና የቤተ ክርስቲያን ፅሑፎች ቀርበዋል።
"ከአሁን በኋላ ከእናንተ የሚጠብቀው ጥያቄ ተፈናቅልናል ዕርዳታ አቅረቡልን ሳይሆን ባለንበት አካባቢ ውሃ አስገቡልን፣ ትምህርት ቤት አስገንቡልን የሚል መሆን አለበት" ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ዳይሬክተርና አክቲቪስት ታማኝ በየነ፡፡
በሥራ ሁኔታ፣ በደመወዝ እና በጤና ሥርዓቱ ውስጥ አሉ ባሏቸው ችግሮች ላይ ጥያቄ ያነሱ ሐኪሞች ባሕር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ቅሬታዎቻቸውን አሰምተዋል።
በክልል የመደራጀት መብትና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በብሄሩ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው የሚፈፀም ጥቃት የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አርብ ዕለት በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የሸክላ ላይ የሥዕል አውደ - ርዕይ በባህር ዳር ተካሄደ፡፡
ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ ዞኖች ተፈናቅለው እየተንገላቱ ላሉ ሰዎች ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ የጌዴኦ አባገዳ ጠየቁ፡፡ አባገዳ ደንቦቢ ማሮ ጥያቄውን ያቀረቡት "ዳራሮ" በሚባለው የጌዴኦ ብሄር ዓመታዊ የምሥጋናና የፀሎት ክብረ በዓል ላይ ነው፡፡ ለተፈናቀሉት ወገኖቻቸው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡
አርቲስት ይሁኔ በላይ ከእንጁባራ ከቪኦኤ ጋር ያደረገው አጭር ቆይታ
የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነው የኦሮሞ ሴቶች "ስንቄ" ባህል የእርቅና የሰላም ተምሳሌት ነው፡፡
የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱንና የህዝበ ወሳኔ ቀን አለመገለፁን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡ ሰልፉ በሲዳማ "ቀጣላ" ባህላዊ ስርዓት የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ ተጠናቅቋል፡
ኢትዮጵያና ኤርትራን በተመለከተ "ዜማችን ፣ ቅዳሴያችንና መዝሙራችን ሰላም ነው" አሉ በሀዋሳ ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የኤርትራ ባህል ቡድን አባላት።
168 የኢትዮጵያ ከተሞች በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት፣ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያከናወኗቸውን ተግባራት በምስል፣ በቅርፅ፣ በባነርና በናሙና አምጥተው እርስ በርስ የሚማማሩበት የከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን አከባበር በከፊል ይሄንን ይመስላል፡፡ ከተለያዩ ከተሞች ለተሳትፎ ወደ ጅጅጋ የሄዱት 10ሺ ገደማ ሲሆኑ የጅጅጋ ከተማም 60 አውቶብሶችን በማዘጋጀት የከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ኤግዚቢሽኑን እንዲጎበኙ ተደርጓል።
“አንድ ዶላር በቀን” የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡት ጥሪ “ወገንዎን በተግባር ለመርዳት ባገኙት መልካም ዕድል የአገርዎን ዕጣ ያሳምሩ።” ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም የኢትዮጵያውያን ተራድዖ ባለ አደራ ቦርድ ሊቀ መንበር
በአማራ ክልል የዳኞች ማኅበር ተቋቋመ
በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ እና ኦነግ መካከል የተዋቀረው የአባ ገዳዎች እና ሽማግሌዎች የዕርቅ ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴ፣ የዕርቅ ሂደቱ ተስፋ ሰጪ መሆኑን እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ውይይት መደረጉን ገለፀ። በሰላም ሥምምነቱ የተኩስ እና ግጭት ማቆም ሥምምነት ቢደርስም ሰዎች በተለያዩ ቦታዎች እየሞቱ የተጠየቁት አቶ ጀዋር እና አቶ በቀለ፣ ችግሩን ተከትሎ ከሁለቱም ወገን ስሞታ እየቀረበ እና
ካለፈው ታኅሣስ ወር ጀምሮ በከፋ ዞን ዴቻ ወረካ 37 ሰላማዊ ዜጎች በታጠቁ ኃይሎች መገደላቸውን ከ20 ሺህ ሕዝብ በላይ መፈናቀሉና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አስታወቀ፡፡
ከትናንት አመሻሹ ጀምሮ ድሬዳዋ ላይ ግጭት ተከስቷል፤ ግጭቱ እስከዛሬ ከሰዓት የዘለቀ ነበር፡፡ በግጭቱ የሞቱና የከፋ ጉዳት የደረሰበት ባይኖርም ቀላል የአካል ጉዳቶችና የንብረት ውድመቶች መከሰታቸው ግን ሪፖርት ተደርጓል፡፡
ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ በማልታ ደሴት አቅራቢያ በሁለት የጀርመን ጀልባዎች ላይ ማረፊያ አጥተው የቆዩ አርባ ዘጠኝ ፍልሰተኞችን እንደሚያስተናግዱ የደሴቲቱ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ጆዜፍ ማስካት ዛሬ አስታወቁ።
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሯል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ ዐብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ነው።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለንግድ ሥራ በአከራይዋቸው ቤቶች ላይ ለጨመረው ኪራይ የእፎይታ ጊዜ መስጠቱን አስታወቀ፡፡ የተጨመረውን መጠን ሙሉ በሙሉ ለመክፈልም የሦስት ዓመት ጊዜ መስጠቱን አስታውቋል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን ይሆናል በተባለው ግዙፍ ፓርቲ ለመዋሃድ ሰማያዊ ፓርቲ የራሱን ግምገማ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ