ዓለም ከፊቷ በተደቀኑ አደገኛ በሽታዎች ሥጋት እየተዋጠች መሆኗን በመግለፅ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት ቻን አሳስበዋል፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ —
በመጭ ወራት ይከተላሉ የተባሉ የጤና ሥጋቶችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ፈጣን የተግባር እርምጃዎች እንዲወሰዱ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማርጋሬት ቻን ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ቻን ይህንን የዓለም ማኅበረሰብ የተቀናጀና ፈጣን እንቅስቃሴ የጠየቁት ለአንድ ሣምንት የሚዘልቀው የድርጅታቸው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጉባዔ ከትናንት በስተያ ሰኞ ጄኔቫ ላይ ሲከፈት ነው፡፡
አንድ ሺህ የሚሆኑ ከመላው ዓለም የተወከሉ የጤና ልዑካን እየተሣተፉበት ባሉት በዚህ ጉባዔ ላይ “ላይቤርያ፣ ሲየራ ሌኦን እና ጊኒ ውስጥ የ11 ሺህ ሰው ሕይወት ከቀጠፈው የኢቦላ ድንበር ዘለል ወረርሽኝ ብርቱ ትምህርት ልንወስድ ይገባናል” ሲሉ ቻን አሳስበዋል፡፡
የዓለሙ የጤና ድርጅት ምላሽ ለመስጠት መድረስ ከነበረበት ጊዜ “ዘግይቷል” እየተባለ የሚወቀስ ሲሆን ድርጅቱ ሊወስድ ይገባ የነበረውን ሙሉ የመቆጣጠሪያ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ኢቦላ ተንሠራፍቶ ዓለምን ማስጨነቅ ጀምሮ እንደነበርም ወቃሾችና ተችዎች ይናገራሉ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5